Moeducation

ትምህርት ሚንስቴር በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን እንደማይመድብ ገለጸ

ትምህርት ሚንስቴር በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን እንደማይመድብ ገለጸ

በትግራይ ክልል ባለው ነባራዊ ሁኔታ በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በክልሉ አስቻይ ሁኔታ እስኪፈጠር በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት እንዲመደቡ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታውቀዋል። ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩና በአሁኑ ወቅት በክልሉ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ትምህርታቸውን መቀጠል ባለመቻላቸው ለቅሬታቸው መፍትሔ ለመጠየቅ በትምህርት ሚኒስቴር ግቢ ከተገኙ ተማሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደገለጹት፣ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ደህንነታቸው ወደሚጠበቅባቸው ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑን ገልጸዋል። ሚኒስትሩ አክለውም፣ ወጣቶች በአሁኑ ወቅት ማተኮር ያለባቸው በትምህርታቸው ላይ በመሆኑና ወደፊት ሀገራቸውን የሚረከቡ ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመዋል።…
Read More