Barbadosjobs

ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ባርባዶስ መላክ ጀመረች

ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ባርባዶስ መላክ ጀመረች

ኢትዮጵያ 12 የጤና ባለሙያዎችን በመንግሥት ለመንግሥት ስምምነት ወደ ባርባዶስ መላኳን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ተናግረዋል። ባለሙያዎቹ በባርባዶስ በሕጋዊ መንገድ የሁለት ዓመት ኮንትራት የተፈራረሙ ሲሆን ለዚሁ ተግባር ከሀገሪቱ መንግሥት ጋር የሥራ ሁኔታ እና የክፍያ ስምምነት መደረጉን ሚኒስትር ዴኤታዋ አንስተዋል። በተጨማሪም "የጤና ባለሙያዎችን በሕጋዊ እና በተደራጀ መንገድ ወደ ውጭ ሀገራት መላክ የሥራ ዕድል ይፈጥራል፤ የባለሙያ ፍልሰትንም በስርዓት ለመምራት ያግዛል" ማለታቸውን አሀዱ ራዲዮ ዘግቧል። አጠቃላይ በአፍሪካ የጤና ባለሙያ እጥረት እና የሥራ አጥነት ችግር መኖሩን ያስታውሱት ሚንስትሯ፤ የስልጠና ስርዓትና የሙያ ፈቃድ አሰጣጥን በሀገራት መካከል ማስተሳሰር የሥራ ዕድል ለማስፋት እንደሚረዳ አስረድተዋል። "የስልጠና እና የሙያ ፈቃድ ስርዓቶች ወጥ እና ተመሳሳይ አለመሆን በባለሙያዎች ላይ እንቅፋት ሲፈጥር…
Read More