Jobs

ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ባርባዶስ መላክ ጀመረች

ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ባርባዶስ መላክ ጀመረች

ኢትዮጵያ 12 የጤና ባለሙያዎችን በመንግሥት ለመንግሥት ስምምነት ወደ ባርባዶስ መላኳን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ተናግረዋል። ባለሙያዎቹ በባርባዶስ በሕጋዊ መንገድ የሁለት ዓመት ኮንትራት የተፈራረሙ ሲሆን ለዚሁ ተግባር ከሀገሪቱ መንግሥት ጋር የሥራ ሁኔታ እና የክፍያ ስምምነት መደረጉን ሚኒስትር ዴኤታዋ አንስተዋል። በተጨማሪም "የጤና ባለሙያዎችን በሕጋዊ እና በተደራጀ መንገድ ወደ ውጭ ሀገራት መላክ የሥራ ዕድል ይፈጥራል፤ የባለሙያ ፍልሰትንም በስርዓት ለመምራት ያግዛል" ማለታቸውን አሀዱ ራዲዮ ዘግቧል። አጠቃላይ በአፍሪካ የጤና ባለሙያ እጥረት እና የሥራ አጥነት ችግር መኖሩን ያስታውሱት ሚንስትሯ፤ የስልጠና ስርዓትና የሙያ ፈቃድ አሰጣጥን በሀገራት መካከል ማስተሳሰር የሥራ ዕድል ለማስፋት እንደሚረዳ አስረድተዋል። "የስልጠና እና የሙያ ፈቃድ ስርዓቶች ወጥ እና ተመሳሳይ አለመሆን በባለሙያዎች ላይ እንቅፋት ሲፈጥር…
Read More
በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ሥራ ማቆማቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ሥራ ማቆማቸው ተገለጸ

ባሳለፍነው ዓመት ሚያዚያ ወር የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ ለማደራጀት ወስኛለሁ ማለቱን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው፡፡ ይህ ግጭት ቀስ በቀስ እያደገ መጥቶ ወደ ጦርነት የተቀየረ ሲሆን የቀድሞው የክልሉ መንግስት በመደበኛ የክልሉ የጸጥታ ሀይል ህግ ማስከበር እንደማይችል እና የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ በደብዳቤ ጠይቋል፡፡ ይህን ተከትሎም ከሀምሌ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ቀናት ጀምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ የነበረ ሲሆን አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት መራዘሙ አይዘነጋም፡፡ በዚህ ጦርነት ምክንትም ከስድስት ሺህ በላይ የሆኑ ሰራተኞች ስራ ማቆም እና ቤተሰቦቻቸውን መመገብ አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ከሥራ ውጭ የኾኑ ዜጎች፣ በግጭቱ ምክንያት…
Read More