17
Sep
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰኑ ይፋ ተደርጓል። ጉባዔው ዲሞክራቲክ ኮንጎ ላይ ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ በተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መቀየሩን የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ጉባኤው አዲስ አበባ ላይ እንዲካሄድ ጥያቄ አቅርቦ በካፍ ተቀባይነት ማግኘቱን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል። በዚህም መሰረት የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በቀጣይ ጥቅምት ወር በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል። ካፍ ዛሬ በሰጠው የቅድመ ጠቅላላ ጉባኤ ጋዜጣዊ መግለጫ የ2024 ቻን አፍሪካ ዋንጫ በሚቀጥለው የካቲት ወር በናይሮቢ ፣ ካምፓላ እና ዳሬ ሰላም እንደሚካሄድ አሳውቋል። የ2024 ቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በጥቅምት እና…