28
Jul
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ አግቢ ሳላሀዲን ሰዒድ ኳስ መጫወት ማቆሙን ገልጿል በአሶሳ ተወልዶ ያደገው ሳላሀዲን ለበርካታ የውጪ እና የሀገር ውስጥ ክለቦች መጫወት ችሏል ሳላሀዲን ሰኢድ ጫማውን ሰቀለ። በተለያዩ ክለቦች እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለበርካታ አመታት በመጫወት የሚታወቀው ገልግሎት ሳላዲን ሰዒድ ጫማውን ሰቅሏል፡፡ ላለፉት 15 ዓመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ አይረሴ ታሪኮችን ያስመዘገበው ሳላዲን እግር ኳስ መጫወቱን እንዳቆመ ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል። ተጫዋቹ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባለፈ ለሙገር ሲሚንቶ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ለሲዳማ ቡና እንዲሁም ከውጪ ደግሞ ለግብጾቹ ዋዲዳግላ እና አልአህሊ፣ ለአልጀሪያው መውሊዲያ አሊደር እና ለቤልጂየሙ ሊርስ እግር ኳስ ክለቦች መጫወት ችሏል። በ37 ዓመቱ ራሱን ከእግር ኳስ ጨዋታ ያገለለው ሳላዲን በተያዘው ዓመት…