23
Oct
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ በይፋ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በ2029 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት አቅም አላት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ጠይቀዋል፡፡ የፊፋ፣ ካፍ እና ሌሎች የእግር ኳስ አመራሮች በአዲስ አበባ በተካሄደው የካፍ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ለዚህ ጉባኤ ተሳታፊዎች ላይ በተዘጋጀ እራት ግብዣ ላይ ንግግር ደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ በይፋ ጠይቀዋል። የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሙትሴፔ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበው፣ የኢትዮጵያውያን ባህል፣እሴትና እንግዳ ተቀባይነት ኢትዮጵያ ቤታችን እንደሆነች እንዲሰማን አድርጎናል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የ2029ኙን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ ከኮሚቴው…