AfCON

ኢትዮጵያ ከኮቲዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆነች

ኢትዮጵያ ከኮቲዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆነች

በኮቲዲቯር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች በመካሄድ ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዚህ ማጣሪያ ጨዋታ አንድ አካል የሆነው ጨዋታ ከማላዊ አቻው ጋር አድርጓል። ይህ ጨዋታ ዜሮ ለዜሮ በሆነ አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኮቲዲቫሩ የአፍሪካ ዋንጫ መውደቁን አረጋግጧል። ምድቡን እየመራች ያለችው ግብጽ አስቀድማ ማለፏን ያረጋገጠች ሲሆን ጊኒ ደግሞ ሁለተኛ በመሆን ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፏን አረጋግጣለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት ውበቱ አባተ በውጤት ማጣት መሰናበታቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከአሰልጣኝ ውበቱ ጋር በስምምነት እንደተለያየ ከዚህ በፊት አስታውቋል። በያዝነው ዓመት ለሚካሄደው የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ኮቲዲቯርን ጨምሮ ከ15 በላይ ሀገራት ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ኮቲዲቯር፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ደቡብ አፍሪካ፣…
Read More
ዋሊያዎቹ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቀኑ

ዋሊያዎቹ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቀኑ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቅንቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በኮትዲቯር አስተናጋጅነት በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ከጊኒ ብሔራዊ ቡድን ጋር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን መጋቢት 15 እና 18 ቀን 2015 ዓ.ም በሞሮኮ ያደርጋል። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ከመጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ልምምዳቸውን ሲያደርጉ ቆይተዋል። ዋልያዎቹ ከትናንት በስቲያ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከሩዋንዳ አቻቸው ጋር ባደረጉት የአቋም መለኪያ ጨዋታ በከነዓን ማርክነህ ግብ 1 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወቃል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አራት ከግብጽ፣ ከማላዊና ከጊኒ ጋር ተደልድሏል፡፡ እስከአሁን…
Read More