06
Apr
የሩሲያ የመኪና አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ሲሆኑ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ ከሩሲያ የላዳ እና ጋዝ ግሩፕ መኪና አምራች ኩባንያዎች የመጡ ተወካዮች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ለተወካዮቹ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ፣ ስለዘርፉ ማበረታቻዎች እንዲሁም በአፍሪካ ግንባር ቀደም ስለሆነው የድሬዳዋ የነጻ ንግድ ቀጠና አጠቃላይ ገለጻ ተደረገላቸዋል፡፡ የመኪና አምራች ኩባንያ ኃላፊዎቹ ከድሬዳዋ በተጨማሪ የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የስራ እንቅስቃሴና የምርት ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ ኩባንያዎቹ በአውሮፓ፣ በደቡብ አሜሪካና የአፍሪካ ገበያዎች ለጤና ተቋማት፣ ለፀጥታ አካላት፣ ለጭነት አገልግሎት እንዲሁም ለግልና ለህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ…