15
Mar
ለአንድ ሳምንት በሚል የተጀመረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። ሩሲያ ከዩክሬን ጎን ቆመው እየተዋጉ ያሉ ቅጥረኛ ወታደሮችን ማንነት ይፋ አድርጋለች። እንደ ሩሲያ መከላከያ ሚንስቴር መረጃ ከሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ከዩክሬን ጎን ሆኖ ሩሲያን እየወጋ ይገኛል ተብሏል። ይህ ኢትዮጵያዊ እስካሁን በህይወት እንዳለ የተገለጸ ሲሆን ወታደሩ ኢትዮጵያዊ ከመሆኑ ውጪ ማንነቱ ይፋ አልተደረገም። በአጠቃላይ ይህ ጦርነት ከተጀመረበት የካቲት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከ89 ሀገራት የተውጣጡ 13 ሺህ 387 ቅጥረኛ ወታደሮች ከዩክሬን ጎን ተሰልፈዋል። ከጠቅላላው ቅጥረኛ ወታደሮች ውስጥም 5 ሺህ 962 ያህሉ በሩሲያ ጦር መገደላቸው ተገልጿል። ፖላንድ ቅጥረኛ ወታደሮችን በማዋጣት ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን 2 ሺህ 960 ዎቹ ተገድለዋል ተብሏል። ከፖላንድ በመቀጠል…