23
Jan
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ለሚኒስትሩ ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል በኢትዮጵያ የኤልክትሪክ መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የመለዋወጫ አካላት ፍላጎትን እንዴት ሊሸፈን ታስቧል? የሚለው ዋነኛው ነበር፡፡ ከኤሌክትሪክ መኪና ውስጥ የባትሪ ጉዳይ ዋናው በመሆኑ ወደ ፊት ለባትሪ የሚወጣው ውጪ ምንዛሪ ፈታኝ እንዳይሆን በሃገር ውስጥ ለማምረት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ምን እየሰራ ነው ሲሉም የምክር ቤቱ አባላት ጠይቀዋል፡፡ አቶ መላኩ በምላሻቸው የኤሌክትሪክ መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች በክልሎችም ጭምር እየጨመረ መምጣቱን መልካም ነው ምክንያቱም ሃገሪቱ በየአመቱ ለነዳጅ የምታወጣውን 4 ቢልዮን ዶላር ያስቀራል ብለዋል፡፡ የኤሌክትሪክ መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች እየበረከቱ…