Economyzones

በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ያሉ ነጋዴዎች ከግብር ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ተወሰነ

በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ያሉ ነጋዴዎች ከግብር ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ተወሰነ

በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ ግብአቶችን እና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተወሰነ:: የገንዘብ ሚኒስቴር ለገቢዎች ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ ምክንያት ከሆኑት መካከል የካፒታል እጥረት፤ የግብአት አቅርቦት ችግር  እና የባለሙያ እጥረት በዋንኛነት ምክንያት አስቀምጧል፡፡ እነዚህን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማቃለል የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ልማትን  ማሳደግ አእንደሚገባ በደብዳቤው ላይ ጠቅሷል፡፡ ግብአቶች እና ሌሎችም ምርቶች በበቂ መጠን ለገበያ እንዲቀርቡ ለማድረግ አስመጪዎች ምርቱን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት የሚከፍሉት ቀረጥ እና ታክስ ውስን የሆነውን ካፒታላቸውን በመያዝ ረገድ የሚያሳድረባቸውን ጫና ማቃለል እንደሚያስፈልግ አስታውቋል። አስመጪዎች  ግብቶችን  እና ምርቶችን ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፍሉ ወደ አገር ውስጥ አስገብተው ለግብአቱ…
Read More