Taxation

በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ያሉ ነጋዴዎች ከግብር ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ተወሰነ

በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ያሉ ነጋዴዎች ከግብር ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ተወሰነ

በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ ግብአቶችን እና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተወሰነ:: የገንዘብ ሚኒስቴር ለገቢዎች ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ ምክንያት ከሆኑት መካከል የካፒታል እጥረት፤ የግብአት አቅርቦት ችግር  እና የባለሙያ እጥረት በዋንኛነት ምክንያት አስቀምጧል፡፡ እነዚህን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማቃለል የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ልማትን  ማሳደግ አእንደሚገባ በደብዳቤው ላይ ጠቅሷል፡፡ ግብአቶች እና ሌሎችም ምርቶች በበቂ መጠን ለገበያ እንዲቀርቡ ለማድረግ አስመጪዎች ምርቱን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት የሚከፍሉት ቀረጥ እና ታክስ ውስን የሆነውን ካፒታላቸውን በመያዝ ረገድ የሚያሳድረባቸውን ጫና ማቃለል እንደሚያስፈልግ አስታውቋል። አስመጪዎች  ግብቶችን  እና ምርቶችን ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፍሉ ወደ አገር ውስጥ አስገብተው ለግብአቱ…
Read More
ኤም-ፔሳ ኢትዮጵያ በአማራ ክልል ግብር የድጅታል ገንዘብ አገልግሎት ለመስጠት ተስማማ

ኤም-ፔሳ ኢትዮጵያ በአማራ ክልል ግብር የድጅታል ገንዘብ አገልግሎት ለመስጠት ተስማማ

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የታክስ ክፍያዎችን በኤም-ፔሳ የዲጂታል ስርዓት ለመሰብሰብ የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ በሆነው ኤምፔሳ_ኢትዮጵያ እና የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ መካከል በባህር ዳር ከተማ ተፈርሟል። ግብር ከፋዮች ከዚህ በኋላ ኤም-ፔሳን በመጠቀም ግብራቸውን ካሉበት ሆነው በዲጂታል አማራጭ በቀላሉ መክፈል ይችላሉ ተብሏል። ከ477 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች ያሉት የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2017 የግብር ዘመን 67 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) ተናግረዋል። በ2018 በጀት ዓመትም ክልሉ 100.37 ቢሊየን ብር የመሰብሰብ እቅድ ያለው ሲሆን ከዚህ ውስጥ እስካሁን 60 በመቶ የሚሆነውን ሰብስቧል ብለዋል። የታቀደውን ገቢ መሰብሰብ የሚቻለው በዲጂታል አማራጭ በመታገዝ ግብርን በቀላሉና…
Read More
ባለፉት 6 ወራት ከ704 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ

ባለፉት 6 ወራት ከ704 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ

ኢትዮጵያዊ ባለፉት ስድስት ወራት እንደ ሀገር ከ704 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ እንደተቻለ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።  አፈጻጸሙ በገቢዎች ሚኒስቴር በግማሽ ዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው 640 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ውስጥ 704 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 110 በመቶ ተሳክቷል ተብሏል። ይህ ገቢ ባለፉት ጊዜያት ለዓመታት ሲሰበሰብ ከነበረው ገቢ ጋር የሚመሳሰል እንደሆነ ተገልጿል። የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ዓመት ስድስት ወራት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር የ63 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ሲሆን ስኬቱ ኢትዮጵያ የውስጥ አቅሟን በማጎልበት እያንሰራራች ለመሆኑ ሁነኛ ማሳያ ተድርጎ የሚወሰድ ነው ሲል መንግሥት አስታውቋል። በግማሽ ዓመቱ ከሀገር ውስጥ ታክስ 362 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን ከውጪ ንግድ…
Read More
ኢትዮጵያ ታማኝ ግብር ከፋዮች በቪአይፒ ኤርፖርት እንዲስተናገዱ ፈቀደች

ኢትዮጵያ ታማኝ ግብር ከፋዮች በቪአይፒ ኤርፖርት እንዲስተናገዱ ፈቀደች

ወርቅ እና ከዚያ በላይ ሽልማት ያገኙ ታማኝ ግብር ከፋዮች በቪአይፒ ኤርፖርት እንዲስተናገዱ መወሰኑ ተገልጿል። ወርቅ እና ከዚያ በላይ ሽልማት ያገኙ ታማኝ ግብር ከፋዮች በቪ.አይ.ፒ ኤርፖርት እንዲስተናገዱ መንግሥት መወሰኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ትናግረዋል። ላለፉት አራት አመታት በታማኝነት ፕላቲኒየም ሽልማት ያገኙ 30 ልዩ ተሸላሚዎች የኢትዮጵያ ዜጎች ከሆኑ፤ የድርጅት ባለቤቶች ወይም ሥራ አስኪያጆች ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንደሚሰጣቸውም ተገልጿል። ይህ የተገለጸው 7ኛው ዙር የታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና መርሃ ግብር በትናንትናው ዕለት በተካሄደበት ወቅት ሲሆን በመርሃ ግብሩ 700 የሚደርሱ ተቋማት እና አልሚ ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል። በዚህም 105 የሚሆኑት በፕላቲኒየም ደረጃ፣ 245 በወርቅ ደረጃ የተቀሩት 350 የሚሆኑት ደግሞ በብር ደረጃ ዕውቅና ያገኙ ናቸው ተሰጥቷቸዋል። ከዚህ…
Read More