Taxbill

መንግስት በቀጣዩ ዓመት 1 ነጥብ 8 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

መንግስት በቀጣዩ ዓመት 1 ነጥብ 8 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

የፌደራል መንግሥት በአዲሱ 2019 በጀት ዓመት አንድ ነጥብ 817 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የ2019 በጀት ዓመት የበጀት መግለጫ ማብራሪያ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት በጥቅሉ አንድ ነጥብ 8 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡ ይህ የገቢ ዕቅድ በ2018 በጀት ዓመት ይሰበሰባል ተብሎ ከተገመተው ጠቅላላ ገቢ አንጻር የ17 ነጥብ 4 በመቶ ዕድገት ያለው ሆኗል። እቅዱ ከዓመታዊ በጀት  ውስጥ የ89  በመቶውን ከታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለመሰብሰብ መታቀዱንም ሚንስትሩ አቶ አህመድ ጠቁመዋል። የታክስ ገቢ ዕቅዱን ለማሳካትም በታክስ ፖሊሲና በታክስ አስተዳደር ረገድ የተያዙ ማሻሻያዎችን፣ የታክስ ዲጂታላይዜሽንና የኤክሳይዝ ስታምፕ…
Read More
ከ10 ዓመት በፊት ለተፈጸመ ታክስ ማጭበርበር ቅጣት እንዲጣል የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ተዘጋጀ

ከ10 ዓመት በፊት ለተፈጸመ ታክስ ማጭበርበር ቅጣት እንዲጣል የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ተዘጋጀ

ማንኛውም ደረሰኝ ሳይቆርጥ የተገበያየ አካል በወንጀል እስከመጠየቅ የሚያደርሰው የተሻሻለው የታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ረቂቁ የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ለ10 ዓመታት ወደኋላ በመሄድ ሂሳቡን በመመርመር ወይም ሂሳብ ኦዲት በማድረግ ተጨማሪ ግብር ማስከፈልን ለገቢ ሰብሳቢው የሚፈቅድ ነው፡፡ ዛሬ ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ የግብር አስተዳደር አዋጅ በተለይ ደረሰኝ ባለመቁረጥ የሚደረግ ግብይት ላይ ከፍ ያለ ቅጣትን የሚያስከትሉ አንቀፆችን የያዘ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ህጋዊ ደረሰኝ ያልሰጠ እንደሆነ በእያንዳንዱ ባልሰጠው ደረሰኝ ልክ 100 ሺህ ብር አስተዳደራዊ ቅጣት በገንዘብ ይቀጣል ይላል የማሻሽያ አዋጁ ማብራሪያ፡፡ በተጨማሪ ይሄንኑ አስተዳደራዊ ቅጣት በዓመት ሁለት ጊዜ የተቀጣ እንደሆነ እና ሆን ብሎ ድርጊቱን መፈፀሙን ከቀጠለ ድርጊቱ እንደ ወንጀል ጥፋት…
Read More