26
Nov
የዘንድሮ ዓመታዊ በጀት ወደ 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር አድጓል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መንግሥት ያቀረበው ተጨማሪ በጀት የተጋነነ ነው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ የፌደራል መንግስት ከስድስት ወር በፊት ለተያዘው በጀት ዓመት 970 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት አጸድቆ ነበር፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት እንዲጸድቅለት በቀረበለት ጥያቄ ዙሪያ መክረዋል፡፡ ተጨማሪ በጀቱ ለዕዳ ክፍያ፣ ለማህበራዊ ድጋፍ፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስተካከያ እንዲሆን መታሰቡን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ ተስፋዬ ቤልጂጌ ተናግረዋል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት መንግስት ያቀረበው ተጨማሪ በጀት የተጋነነ ነው ሲሉ ተቃውሞ ቅርበዋል፡፡ ይሁንና ከ2017 አስከ 2021 ድረስ የተነደፈውን የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፊስካል ፖሊሲ ማዕቀፍ…