08
Jun
በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት የሀገር መከላከያ በጀት ወጪ ከ120 ቢሊዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን ይህም በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል። ለ2016 በጀት ዓመት ከቀረበው 801 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት በጀት ውስጥ ለመከላከያ ሚኒስቴር 50 ቢሊዮን ብር ሲመደብ ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የወደሙ ተቋማትና አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ደግሞ 20 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙ ተገልጿል። በ2015 በጀት ዓመት ውስጥ አጠቃላይ ከተበጀተው የመከላከያ ሚኒስቴር በጀት ድርሻ ከ12 ቢሊዮን በላይ ብር ደርሷል ተብሏል። የሰሜኑ ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መፍትሔ ማግኘቱን ተከትሎ መከላከያ ሚኒስቴር ለ2016 በጀት ዓመት 50 ቢሊዮን ብር እንደተያዘለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቀረበው የቀጣዩ ዓመት ረቂቅ በጀት ለመረዳት ተችሏል።…