08
Jun
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመንግሥት በጀት የ281 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንደገጠመው የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ አስታውቀዋል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 በጀት ዓመት የመንግሥት በጀት 801.65 ቢሊዮን ብር እንዲሆን፤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ምክር ቤቱ የቀረበውን የበጀት ረቂቅ እየገመገመ ነው፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፤ መንግሥት ለ2016 ካረቀቀው አጠቃላይ በጀት ውስጥ የ281 ቢሊዮን ብር ጉድለት ማጋጠሙን ጠቁመዋል፡፡ የዓመቱ የበጀት ጉድለት በመጠናቀቅ ላይ ከሚገኘው የ2015 በጀት ዓመት የበጀት ጉድለት 50 ቢሊዮን ብር ገደማ ሆኗል፡፡ የ2015 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀት 786 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፤ የበጀት ጉድለቱ 231 ቢሊዮን ብር መሆኑን ሚኒስትሩ…