Newtaxdraft

ደረሰኝ የማይሰጡ ነጋዴዎች የ100 ሺህ ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተባለ

ደረሰኝ የማይሰጡ ነጋዴዎች የ100 ሺህ ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተባለ

በግብይት ወቅት ማናቸውም ግብር ከፋይ ነጋዴ ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲያከናውን ወይም ዋጋ አሳንሶ የተገኘ በእያንዳንዱ ደረሰኝ የአንድ መቶ ሺህ ብር ቅጣት መጣል የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። ያለ ደረሰኝ ሲገበያይ የተገኘ ማንኛውም ግብር ከፋይ ለገዢ ባልሰጠው በእያንዳንዱ ደረሰኝ ብዛት ከዚህ ቀደም 50 ሺህ ብር ይቀጣ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ማሻሻያ በተደረገለት የታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ መሰረት ወደ አንድ መቶ ሺህ ብር ቅጣት ከፍ ብሏል።የገንዘብ ሚኒስቴር እንደ ዋና ማሻሻያዎች ካነሳቸው መካከል የታክስ የምስክር ወረቀት አሰጣጥን ማሻሻል፣ የታክስ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ በማስታረቅ ሥርዓት መፍታት፣ የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ የሚታረምበትን ሥርዓት ግልጽ ማድረግ፣ እንዲሁም የውሳኔ ማስታወቂያ ማሻሻያና የይግባኝ ማቅረቢያ የጊዜ ገደቦችን በግልጽ ማስቀመጥ የሚሉት ይገኙበታል።እነዚህ…
Read More