LNG

በተፈጥሮ ጋዝ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች አዲስ አስገዳጅ ደረጃዎች መውጣቱ ተገለጸ

በተፈጥሮ ጋዝ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች አዲስ አስገዳጅ ደረጃዎች መውጣቱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ መጠቀም መጀመሯን ተከትሎ አስገዳጅ ደረጃዎች ማዘጋጀቱን ገልጿል። የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት በቀለ በሰጡት መግለጫ 79 አጠቃላይ ደረጃዎችን መዘጋጀታቸውን ገልጸው ከዚህ ውስጥ ሰባቱ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ደረጃዎች እንደሆኑ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በሀገር ውስጥ ለሚገጣጠሙ እና ከውጭ ለሚገቡ በነዳጅ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ደረጃዎች እንዳሏት የተናገሩት ዶክተር መሰረት በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ግን የሚመዘኑበት የጥራት ማስጠበቂያ ደረጃ እንዳልነበራት አክለዋል፡፡ አዲሱ ደረጃ የተፈጥሮ ጋዝ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡም ሆነ በሀገር ውስጥ ሲገጣጠሙ ሊሟሉ የሚገቡ መስፈርቶችን የያዘ እንደሆነም ተገልጿል። በኢንስቲትዩቱ የደረጃዎች ዝግጅት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ይልማ መንግስቱ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ጥራት ለማስጠበቅ የወጣው ደረጃ በሶማሊ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ መጠቀም በመጀመሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ አዲሱ ደረጃ የተፈጥሮ ጋዝ የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ምን ምን መስፈርቶችን ማሟላት እንደሚገባቸው…
Read More
ኢትዮጵያ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር የሚያመርት የጋዝ ማጣሪያ አስመረቀች

ኢትዮጵያ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር የሚያመርት የጋዝ ማጣሪያ አስመረቀች

በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር የሚያመርተው የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ተመርቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀናል ብለዋል። በተመሳሳይ በዓመት 1 ነጥብ 33 ቢሊየን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን የነዳጅ ማጣሪያ ስራ ማስጀመራቸውንም ገልጸዋል፡፡ ማጣሪያው ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1 ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ፕሮጀክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ…
Read More