ogadengasoil

ኢትዮጵያ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር የሚያመርት የጋዝ ማጣሪያ አስመረቀች

ኢትዮጵያ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር የሚያመርት የጋዝ ማጣሪያ አስመረቀች

በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር የሚያመርተው የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ተመርቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀናል ብለዋል። በተመሳሳይ በዓመት 1 ነጥብ 33 ቢሊየን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን የነዳጅ ማጣሪያ ስራ ማስጀመራቸውንም ገልጸዋል፡፡ ማጣሪያው ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1 ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ፕሮጀክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ…
Read More
ኢትዮጵያ የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ የመላክ እቅዷን ሰረዘች

ኢትዮጵያ የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ የመላክ እቅዷን ሰረዘች

መንግስት  ከኦጋዴን ተፋሰስ የተፈጥሮ ጋዝ በጅቡቲ በኩል በቧንቧ መስመር ወደ ውጭ የመላክ እቅዱን የገንዘብ እጥረትና የትግበራ መጓተትን በመጥቀስ በይፋ ሰርዟል። በኢትዮጵያ ኢነርጂ አውትሉክ 2025 የተረጋገጠው ይህ ስረዛ፣ በሀገራዊ የኢነርጂ ፖሊሲ ውስጥ ትልቅ ለውጥ የሚያሳይ ሲሆን፣ ከውጭ የመላክ ፍላጎት ወደ ሀገር ውስጥ አጠቃቀም እየተሸጋገረ መሆኑን ያመለክታል ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። “የኢትዮጵያ መንግስት በኦጋዴን ክልል የታቀደውን የተፈጥሮ ጋዝ ማውጣት እና የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ ለመላክ ወደ ጅቡቲ የሚዘረጋውን የቧንቧ መስመር ፕሮጀክት ሰርዟል” ሲል ሪፖርቱ ይገልጻል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በጋራ የተዘጋጀው የኢነርጂ አውትሉክ “የፕሮጀክት ፋይናንስን በማግኘት ረገድ ያሉ ችግሮች እና የፕሮጀክት ትግበራ…
Read More