Gasoil

ኢትዮጵያ የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ የመላክ እቅዷን ሰረዘች

ኢትዮጵያ የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ የመላክ እቅዷን ሰረዘች

መንግስት  ከኦጋዴን ተፋሰስ የተፈጥሮ ጋዝ በጅቡቲ በኩል በቧንቧ መስመር ወደ ውጭ የመላክ እቅዱን የገንዘብ እጥረትና የትግበራ መጓተትን በመጥቀስ በይፋ ሰርዟል። በኢትዮጵያ ኢነርጂ አውትሉክ 2025 የተረጋገጠው ይህ ስረዛ፣ በሀገራዊ የኢነርጂ ፖሊሲ ውስጥ ትልቅ ለውጥ የሚያሳይ ሲሆን፣ ከውጭ የመላክ ፍላጎት ወደ ሀገር ውስጥ አጠቃቀም እየተሸጋገረ መሆኑን ያመለክታል ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። “የኢትዮጵያ መንግስት በኦጋዴን ክልል የታቀደውን የተፈጥሮ ጋዝ ማውጣት እና የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ ለመላክ ወደ ጅቡቲ የሚዘረጋውን የቧንቧ መስመር ፕሮጀክት ሰርዟል” ሲል ሪፖርቱ ይገልጻል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በጋራ የተዘጋጀው የኢነርጂ አውትሉክ “የፕሮጀክት ፋይናንስን በማግኘት ረገድ ያሉ ችግሮች እና የፕሮጀክት ትግበራ…
Read More
ኢትዮጵያ ከሁለት ወር በኋላ ነዳጅ ለገበያ እንደምታቀርብ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከሁለት ወር በኋላ ነዳጅ ለገበያ እንደምታቀርብ ተገለጸ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዳጅ ለገበያ እንደምታቀርብ መናገራቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘግቧል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ካሉ የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ከመስከረም ወር ጀምሮ ነዳጇን ለገበያ ማቅረብ እንደምትጀምር ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰባት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ነዳጅ ማውጣት ጀመረች በሚል ለኢትዮጵያዊያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡ ይሁንና ይህ ከሆነ ከሰባት ዓመት በኋላ ኢትዮጵያ ነዳጅ ለገበያ እንደምታቀርብ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በሶማሊ ክልል ኦጋዴን አካባቢ ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ እንዳላት በተደጋጋሚ ሲገለጽ የቆየ ሲሆን የቻይና ፖሊሲጂኤል ኩባንያ ነዳጅ ለማውጣት በሂደት ላይ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ የነዳጅ ፍላጎቷን ሙሉ ለሙሉ…
Read More
ኢትዮጵያ አዲስ የነዳጅ ማደያ ፈቃድ መስጠት አቆመች

ኢትዮጵያ አዲስ የነዳጅ ማደያ ፈቃድ መስጠት አቆመች

በመላው ሃገሪቱ የነዳጅ ማደያ ፍቃድ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱ ተገለጿል፡፡ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አሁን ላይ የነዳጅ ማደያ ማስፋፊያ ፍቃድ ሙሉ ለሙሉ አስታውቋል፡፡ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ እንደተናገሩት መንግስት የነዳጅ ማደያ ማስፋፊያን የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡ መንግስት የነዳጅ ማደያዎችን በሀገር ውስጥ ለማስፋፋት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ አሁን ላይ ግን ባልተፈለገ አቅጣጫ እየሄደ መሆኑን ባለስልጣኑ በማረጋገጡ ፍቃዱ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲታገድ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ባለስልጣኑ ጥናት እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት ወ/ሮ ሳህረላህ የማደያዎች ፍቃድ አሰጣጥ እና ተደራሽነት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሄ ካገኙ በኋላ ፍቃድ የመስጠቱ ስራ ዳግም እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡ ችግሩ ከተፈታ በኋላ በተለይም የነዳጅ…
Read More