Housing

መንግስት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን መቆጣጠር የሚያስችለውን ህግ አወጣ

መንግስት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን መቆጣጠር የሚያስችለውን ህግ አወጣ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅን አጽድቋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ አጽድቋል። በምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተስፋዬ በልጂጌ ለምክር ቤቱ አባላት በሰጡት ማብራሪያ፤ መንገግስት የዜጎች መሰረታዊ ፍላጎት የሆነውን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ለማሻሻል የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ ቢሆንም፤ ከመኖሪያ ቤት ፍላጎት ጋር ሊጣጣም አልቻለም ብለዋል። አቶ ተስፋዬ አክለውም ፤ በኢትዮጵያ የተጋነኑ እና ከተከራዮች የመክፈል አቅም በላይ የሆነ የቤት ኪራይ ጭማሪዎች በከተሞች እንዳሉ ተናገረዋል፡፡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ በተለይ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የከተማ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እያስነሳ እና ዜጎችም ተረጋግተው ኑሯቸውን…
Read More
በአዲስ አበባ 100 ሺህ ቤቶችን በአንድ ዓመት ውስጥ ለመገንባት ስምምነት ተፈረመ

በአዲስ አበባ 100 ሺህ ቤቶችን በአንድ ዓመት ውስጥ ለመገንባት ስምምነት ተፈረመ

የቤቶቹ ግንባታ በ68 የሪል ኢስቴት አልሚዎች እንደሚገነባ የተገለጸ ሲሆን መንግሥት መሬት በነጻ ለማቅረብ ተስማምቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግሥትና በግል አጋርነት ፕሮጀክት አማካይነት በመረጣቸው ሪል ስቴት አልሚዎች፣ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ወጪ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሊካሄድ ነው ተብሏል። በዚህ ፕሮግራም ሥር እንዲሳተፉ 68 ሪል ስቴት አልሚዎችን የመረጠ ሲሆን፤ አልሚዎቹም በተቀመጠው 70/30 አጋርነት መሠረት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተጣምረው ግንባታውን ለማካሄድ ውል መግባታቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ከእነዚህም አልሚዎች ውስጥ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ኦቪድ ግሩፕ፣ ፍሊንትስቶን ሆምስ፣ እንይ ኮንስትራክሽን፣ ጊፍት ሪል ስቴትና ሌሎችም ይገኙበታል። የከተማ አስተዳደሩ የቤቶቹን ግንባታ ለማካሄድ የሚያስፈልገውን መሬት ከሊዝ ነፃ ማቅረብና መሠረተ ልማቶችን የማሟላት ኃላፊነት አለበት ተብሏል። የሪል ስቴድ ድርጅቶች…
Read More