22
Aug
ከፌዴራልና ከክልል በአጠቃላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሪል እስቴት ልማት ዘርፍ ለመሳተፍ ፈቃድ የወሰዱና የተመዘገቡ 6 ሺሕ የሚሆኑ አልሚዎች ያሉ ቢሆኑም፤ በሥራ ላይ የሚገኙት ግን ከ400 እንደማይበልጡ የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር አስታውቋል። የሪል እስቴት ዘርፉ ከአልሚዎች፣ ከገዢዎችና ከፋይናንስ ተቋማት ጨምሮ፤ በርካታ ችግሮች እና ተነሳሽነት ያልነበረበት እንደነበር የገለጹት፤ የማህበሩ ም/ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጀበል ጀማል ናቸው። ያለውን ችግር ለማስተካከልና በዘርፉ መተጋገዝ ካለና በጋራ መስራት ከተቻለ፤ የተሻለ ለውጥ ሊመጣ እንደሚችል በማመን የሪል እስቴት አልሚዎች ማሕበር መመስረት መቻሉንም አንስተዋል። ማሕበሩ ከመንግሥትና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በ29 አባላት መመስረት እንደቻለ አስታውሰው፤ አሁን ላይ ከ100 በላይ አባልትን በውስጡ መያዙን ገልጸዋል። አሁን ላይ እንደሀገር ከተመዘገቡት 6 ሺሕ…