Business

ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን መጠቀም ጀመረች

ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን መጠቀም ጀመረች

የሶማሌላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስቴር ዛሬ በሶማሌላንድ በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎች ስራ መጀመራቸውን ገልጿል። የሶማሌላንድ የንግድና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አብዲረሺድ ኢብራሂም ደግሞ  "የሶማሌላንድ መንግሥት በበርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎችን ስራ አስጀምሯል " ሲል ይፋ አድርገዋል። "ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ምዕራፍ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ይህ ውጥን ቀጠናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ሶማሌላንድ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉ አክለዋል። ቢሮው በወደቡ የሚራገፉ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ መዳረሻዎች እንዲጓጓዙ የሚያሳልጥ ነውም ተብሏል። በርበራ ወደብ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትሱ DP World ይተዳደራል የተባለ ሲሆን የበርበራ ወብ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስፓቺ ዋታንቫራቺ ተገኝተው…
Read More
ዳሸን ባንክ ዘ ባንከር የተሰኘውን ሽልማት አሸነፈ

ዳሸን ባንክ ዘ ባንከር የተሰኘውን ሽልማት አሸነፈ

ዳሸን ባንክ በተለያዩ ዘርፎች ባስመዘገበው የላቀ አፈጻፀም የ“ዘባንከር” ሽልማት ተሸላሚ ሆነ ባንኮችን በተለያዮ የምርጥ አፈጻጸም መለኪያዎች የሚመዝነው የእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ የሚያሳትመው ዘባንከር መጽሔት ዳሸን ባንክ የ2024 የኢትዮጵያ አሸናፊ ሆኗል፡፡  የዳሸን ባንክ ቺፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን ወ/ሪት እየሩሳሌም ዋጋው እና የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የፋይናንስ ዘርፍ አማካሪ አቶ ሙሉጌታ አለባቸው በእንግሊዝ ሎንዶን ተገኝተው ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡  በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለፀው ዳሸን ባንክ በዘርፉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማቅረብ እና ከተለያዩ አለምአቀፍና አህጉራዊ ባለድርሻ አካላት ጋር የፈጠረው ውጤታማ ጥምረት ለሽልማት አብቅቶታል ተብሏል፡፡  አቶ ሙሉጌታ አለባቸው በስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ሽልማቱ ዳሸን ባንክ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አማካኝነትና እና ከተለያዩ አለም አቀፍና አህጉራዊ ተቋማት…
Read More
ኢትዮጵያ 10 የኢንዱስትሪ ፓርኮቿን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንነት አሳደገች

ኢትዮጵያ 10 የኢንዱስትሪ ፓርኮቿን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንነት አሳደገች

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስፈላጊዉን መስፈርት አሟልተዋል ያላቸዉን 10 ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን እንዲያድጉ መወሰኑ ተገልጿል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በበኩሉ እንዳስታወቀው በስሩ ከሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና መካከል 10ሩ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማደጋቸውን አሳዉቋል። አሁን በስራ ላይ ካሉ 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ያደጉት አዳማ ባህርዳር ፣ ቦሌ ለሚ ፣ ደብረ ብረሃን እና ሀዋሳ ፣ ጅማ ፣ ቂሊንጦ ፣ ኮምቦልቻ ፣ መቀሌ እና ሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መሆናቸው ታዉቋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለማሳደግ አዋጅ ቁጥር 1322/2016 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል። ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ…
Read More
28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተጭበርበሩ

28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተጭበርበሩ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የባንኩ ሪፖርት እስከ ሰኔ 2024 ድረስ ያሉ የገንዘብ እንቅስቀሴዎች ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል፡፡ ባንኩ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው 28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በአጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን አጥተዋል ብሏል፡፡ የማጭበርበር ድርጊቶቹ የተፈጸሙት በሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች፣ በተሰረቁ የኤትኤም ማሽኖች፣ በሐሰተኛ ቼኮች፣ በሐሰተኛ የስልክ መልዕክት እና ተያያዥ መንገዶች አማካኝነት ነው፡፡ በዚህ ዓመት ባንኮች ያጡት ገንዘብ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ300 ሚሊዮን ብር ጭማሪ እንዳሳየም በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ካሉ 31 ባንኮች ውስጥ 28ቱ ሲጭበረበሩ የቀሪዎቹ ሶስት ባንኮች ማንነት ግን በሪፖርቱ ላይ አልተጠቀሰም፡፡ ባንኮች ከአነስተኛ የብድር እና ቁጠባ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ብድሮችን እየሰጡ…
Read More
ኢትዮጵያ 251 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከአይኤምኤፍ አገኘች

ኢትዮጵያ 251 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከአይኤምኤፍ አገኘች

ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ 251 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር እንደሚለቅ አስታውቋል፡፡ ተቋሙ እንዳስታወቀው ብድሩን ለመልቀቅ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ከስምምነት ላይ ደርሷል። ድርጅቱ ብድሩን ለማጽደቅ የተስማማው፣ የድርጅቱ የባለሙያዎች ቡድን ከኅዳር 3 እስከ 17 በአዲስ አበባ ተገኝቶ ኹለተኛውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ግምገማ ማድረጉን ተከትሎ ነው። የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ፣ የብድር መልቀቅ ስምምነቱን በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ እንደሚያጸድቀውና ወደፊት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ግምገማዎች በየስድስት ወሩ እንደሚካሄዱ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል። የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደተቀረፈና በመደበኛውና በትይዩ የውጭ ሀገራት መገበያያ ምንዛሬዎች መካከል ያለው ልዩነት ከ10 በመቶ በታች መውረዱን የጠቀሰው ድርጅቱ፣ መንግሥት ጥብቅ የገንዘብና ፊስካል ፖሊስ እንዲቀጥል አሳስቧል። ኢትዮጵያ ካሳለፍነው ሐምሌ ወር ጀምሮ በአይኤምኤፍ እና…
Read More
የፌደራል መንግስት 582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ዓመታዊ በጀት አስጸደቀ

የፌደራል መንግስት 582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ዓመታዊ በጀት አስጸደቀ

የዘንድሮ ዓመታዊ በጀት ወደ 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር አድጓል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መንግሥት ያቀረበው ተጨማሪ በጀት የተጋነነ ነው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ የፌደራል መንግስት ከስድስት ወር በፊት ለተያዘው በጀት ዓመት 970 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት አጸድቆ ነበር፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት እንዲጸድቅለት በቀረበለት ጥያቄ ዙሪያ መክረዋል፡፡ ተጨማሪ በጀቱ ለዕዳ ክፍያ፣  ለማህበራዊ ድጋፍ፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስተካከያ እንዲሆን መታሰቡን  በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ ተስፋዬ ቤልጂጌ ተናግረዋል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት መንግስት ያቀረበው ተጨማሪ በጀት የተጋነነ ነው ሲሉ ተቃውሞ ቅርበዋል፡፡ ይሁንና ከ2017 አስከ 2021 ድረስ የተነደፈውን የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፊስካል ፖሊሲ ማዕቀፍ…
Read More
ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ምርቶች መጠቀምን የሚከለክል ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ምርቶች መጠቀምን የሚከለክል ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ ለአንድ ጊዜ ግልጋሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶች ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክል ህግ አዘጋጀች፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፕላስቲክ ምርቶች አጠቃቀም ላይ ገደብ የሚጥል ረቂ ህግ ላይ ተወያይቷል፡፡ ምክር ቤቱ ባሳለፍነው ሳምንት ለአንድ ጊዜ ግልጋሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅን አዘጋጅቷል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ለዝርዝር እይታ እና ተጨማሪ ግብዓት ታክሎበት እንዲጸድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቷል። ረቂቅ አዋጁ የሀገሪቱን የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ፣ ማጓጓዝ፣ ክምችት፣ መልሶ አጠቃቀም፣ መልሶ ኡደት እና አወጋገድ ሥርዓት ማስያዝ ላይ ያተኮረ እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ በበኩላቸው ለሀገሪቱ ፓርላማ የተመራው ይህ ረቂቅ አዋጅ፤…
Read More
ኢትዮጵያ በሶስት ወራት ውስጥ ከ87 ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገራት መላኳ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በሶስት ወራት ውስጥ ከ87 ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገራት መላኳ ተገለጸ

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የሶስት ወራት እቅድ አፈጻጸማቸውን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 140 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ ለመላክ ታቅዶ ነበር ብለዋል፡፡ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በዘንድሮ በጀት ዓመት 700 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ ለመላክ እቅድ እንደነበረውም ሚኒስትሯ አክለዋል፡፡ ተቋሙ በ2016 በጀት ዓመት 332 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ መላካቸውም ተገልጿል። ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የተላከባቸው ሀገራት ስድስት የመካከለኛው ምስራቅ እና ሁለት የአውሮፓ ሀገራት ናቸው።  ሀገራቱ “የሰለጠኑ” እና “በከፊል የሰለጠኑ” ሰራተኞችን ከኢትዮጵያ እንደሚፈልጉ የጠቆሙት ሙፈሪያት፤ በጤና፣ በምህንድስና፣ በአርክቴክቸር፣ በሆቴል እና መስተንግዶ ዘርፎች፣ በኤሌክትሪክ እና ቧንቧ ስራዎች እንደዚሁም…
Read More
ኢሰማኮ ለሰራተኞች የሥራ ግብር እንዲቀነስ ጠየቀ

ኢሰማኮ ለሰራተኞች የሥራ ግብር እንዲቀነስ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ እንዳሉት በቋሚ ደመወዝ ለሚተዳደሩ ሰራተኞች የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ ሌሎች የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን በደብዳቤ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ እንደገለጹት ከብር የመግዛት አቅም መዳከም ጋር ተያይዞ ቋሚ ደመወዝ የሚያገኙ ሰራተኞች ለከፍተኛ የኑሮ ውድነት መዳረጋቸውን ገልጸዋል። "በተለይም ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኘው ሰራተኛ ቀን ቀን እየሠራ ማታ ማታ ሆቴሎች ላይ ፍርፋሪ እየለመነ እያደረ ነው።" ያሉት ፕሬዝዳንቱ የኑሮ ጫናው በተለይ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተቀጥረው በሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። አክለውም ከዚህ በፊት በሰራተኞች የኑሮ ሁኔታ ዙርያ ከጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ጋር ተደጋጋሚ  ውይይቶች መደረጋቸውን አስታውሰው ነገር ግን እነዚህ ውይይቶች ውጤት…
Read More
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ማደጉ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ማደጉ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከባንኮች የውጭ ንግድ ግብይት ብቻ በየወሩ 500 ሚሊዮን ዶላር እያገኘች እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ካሳለፍነው ሐምሌ ወር ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲመራ ማድረጓ ይታወሳል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከወጪ ንግድ ብቻ በወር በአማካይ 500 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡ ዋና ገዢው አክለውም የባንክ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በፊት ከነበረበት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ወደ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ማደጉንም ገልጸዋል፡፡ አቶ ማሞ አክለውም ከኹለት ሳምንት በፊት በባንኮች መካከል በተጀመረው የእርስ በርስ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግብይት እንደተካሄደም ተናግረዋል። የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ ሀገራት…
Read More