Iranisraelwar

በአዲሱ የነዳጅ አቅርቦት መመሪያ መሰረት ቅድሚያ የሚሰጣቸው እነማን ናቸው?

በአዲሱ የነዳጅ አቅርቦት መመሪያ መሰረት ቅድሚያ የሚሰጣቸው እነማን ናቸው?

የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለሥልጣን በመካከለኛው ምስራቅ ያጋጠመውን ጦርነት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ለመቋቋም በአገር ውስጥ የነዳጅ ስርጭት እና ግብይት ላይ ጥብቅ የቁጠባ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የሚያዝ አዲስ መመሪያ አውጥቷል። በመመሪያው መሠረት የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ለማንኛውም የነዳጅ ዓይነት አቅርቦት ቅድሚያ እንዲሰጡ ያላቸውን አካላት ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ለፀጥታ ተቋማት፣ ቁልፍ ለሆኑ የመንግስት ፕሮጀክቶች እና በተለይም በመጠናቀቅ ላይ ላሉ የልማት ስራዎች ቅድሚያ እንዲሰጣቸው አዟል። ለኢንዱስትሪዎች፣ መሠረታዊ ሸቀጦችን ለሚያመርቱ አምራች ድርጅቶች እና ምርታቸውን ወደ ውጭ ለሚልኩ ተቋማትም ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ከተባሉ አካላት መካከል ናቸው። እንዲሁም ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለሚታይባቸው እና የሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት ፍሰት ላለባቸው የኮሪደር አካባቢዎች እና ለሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች…
Read More
የእስራኤል- ኢራን ጦርነት ለነዳጅ ድጎማ የሚወጣውን ገንዘብ ጨምሮታል ተባለ

የእስራኤል- ኢራን ጦርነት ለነዳጅ ድጎማ የሚወጣውን ገንዘብ ጨምሮታል ተባለ

ኢትዮጵያ ለነዳጅ ግዢ በየዓመቱ ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ወጪ እንደምታደርግ ተገልጿል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ መጋቢት 2፣ 2018 በሰጡት መግለጫ በእስራኤል-አሜሪካ እና ኢራን መካከል በተጀመረው ጦርነት ምክንያት ለነዳጅ ድጎማ የሚያወጣው ወጪ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል፡፡ እንደ አቶ አህመድ ገለጻ ይህ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ኢትዮጵያ አንድ ሊትር ቤንዚን በ129 ብር ለተጠቃሚዎች ስታቀርብ የነበረ ሲሆን ድጎማው ቢቀር ግን የአንድ ሊትር ቤንዚን መሸጫ ዋጋ 157 ብር ይሆን ነበር፡፡ እንዲሁም ነጭ ናፍጣ 129 ነበር በሊትር ሲሸጥ ነበር የተባለ ሲሆን ድጎማው ቢነሳ 182 ነጥብ 8 ብር መሸጥ ነበረበት ተብሏል፡፡ ሚኒስትሩ አክለውም በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ኢትዮጵያ ቤንዚን የ28 ነጥብ…
Read More
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢራንን ጥቃት አወገዙ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢራንን ጥቃት አወገዙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እሁድ ዕለት ኢራን በኩዌት ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ ከኩዌት ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ሳባህ ኻሊድ አል ሀማድ አል ሳባህ ጋር በስልክ መወያየታቸው ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኩዌቱ ልዑል አልጋ ወራሽ ጋር ባደረጉት ውይይት በአገሪቱ ሉዓላዊ ግዛት እና የአየር ክልል ላይ የሚፈጸም ጥቃትን በጽኑ ማውገዛቸውን የኩዌት የዜና ወኪል ዘግቧል። ይህ በዚህ እንዳለም ኢራን በእስራኤል እና አሜሪካ በደረሰባት የአየር ላይ ጥቃት የአጸፋ እርምጃ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ በምትወስዳቸው እርምጃዎች ኢትዮጵያዊን መጎዳታቸው እየተገለጸ ይገኛል፡፡ በመቶ ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊን እስራኤልን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ተቀጥረው በመስራት ላይ ሲሆኑ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬት፣ ኳታር፣ ኩዌት እና ባህሬን ብዙ ኢትዮጵያዊያን ይኖራሉ፡፡ ኢራን…
Read More