06
Aug
በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል። እስራኤል የሃመስ መሪ ኢስማኤል ሃኒየህ እና የሊባሱ ሄዝቦላህ የጦር መሪ ፉአድ ችኩር መግደሏን ተከትሎ ኢራን በእስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች። የኢራንን ዛቻ ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ከፍተኛ ስጋት በመንገሱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረጉ በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን ሀገራትም ዜጎቻቸውን በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው። በቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ የቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፤ በሊባኖስ እና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ ስጋት እና ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መምጣቱን አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ለማስጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በትኩረት እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና…