05
Oct
ለፍልስጤም ነጻነት የሚታገለው ሐማስ በእራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረው ጦርነት አንድ ዓመት ሞልቶታል፡፡ ይህ ጦርነት ወደ ሊባኖስ መስፋፋቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ ዓለማችን አየር መንገዶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚያደርጓቸውን በረራዎች አቋርጠዋል፡፡ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደ ቤይሩት እና ወደ ቴልአቪቭ የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት ማቋረጡን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል። አየር መንገዱ በድረገ ገጹ ባጋራው መረጃ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስከሚያወጣ ድረስ ወደ ቤይሩት የሚያደርጋቸውን ሁሉንም በረራዎች ማቋረጡን ገልጿል። ወደ ቴልአቪቭ ደግሞ እስከ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በረራ የማያደርግ መሆኑን ነው አየር መንገዱ የገለጸው። በተጠቀሱት አካባቢዎች ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የጠቀሰው አየር መንገዱ፤ ስለጉዳዩ…