ጣልያን በኢትዮጵያ የባቡር መስመር ግንባታ ለማድረግ ተስማማች

የጣልያን ባቡር ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት የተቋረጠውን የአዋሽ- ኮምቦልቻ እና ሐራ ገበያ የባቡር መስመርን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ቁርጠኝነት አለኝ ብሏል።

የአዋሽ- ኮምቦልቻ እና ሐራ ገበያ  የባቡር መስመርን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ የመንግስት ቁርጠኝነት ምኖሩን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑ የህግ አገልግሎት ሃላፊ አቶ ካሳሁን ሙላቱ እንደገልፁት ኮርፖሬሽኑ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማጠናከር ከኮይፓ ኢጣሊያ ጋር ስምምነት አድርጓል።

ስምምነቱ አዳዲስ የባቡር መስመሮችን መዘርጋትን እንዲሁም እየተገነቡ ያሉ የባቡር መስመሮችን በፍጥነት አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባትን የሚያካትት ነው ብለዋል።

ከዛም ባለፈ በጋራ ድርጅቶችን ማቋቋም እንዲሁም ትላልቅ ዎርክ ሾፖሽን ማሻሻል ጨምሮ በርካታ ስትራቴጂካዊ ስራዎች የሚሰራበት የጋራ ስምምነት መሆኑን ገልፀዋል።

ስምምነቱ  በተለይም የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ ትኩረት ያደርጋል ያሉት አቶ ካሳሁን የአዋሽ- ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ  የባቡር መስመር ፕሮጀክት ተጠናቆ ወደ አገልግሎት የሚገባበት ሁኔታ ላይ የሚያተኩር መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ አቶ ካሳሁን ገለፃ ፕሮጀክቱን ዳግም ለማስጀመር ሰፊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው። 

በተደረገው የማዕቀፍ ስምምነት መሰረትም መንግስት በፕሮጀክቱ ያጋጠሙ ጉዳቶችን በመለየት በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባ የማድረግ ከፍተኛ ቁርጠኝነት አለው ብለዋል።

ስምምነቱ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ብቻ ሳይሆን ከተጠናቀቁ በኋላ በምን አይነት መንገድ አገልግሎት መስጠት እንዳለበት የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት መሆኑንም አመላክተዋል።

የባቡር መሰረተ ልማትን  ከኢንዱስትሪዎች ጋር እንዲሁም ከሎጀስቲክ ማዕከላት ጋር የማገናኘት ስራም ይሰራል ተብሏል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *