30
Jan
በጣልያን-አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ይህችን አውሮፕላን መረከባቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት "ፀሐይ" አውሮፕላንን ከጣልያን መንግሥት በይፋ መረከባቸውን አስታውቀዋል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ ላለፈው አንድ አመት የአውሮፕላኑን መመለስ ስራ እንዳገዙም ተገልጿል። "ፀሐይ" እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1935 ዓ.ም በጀርመናዊው ኢንጂነር እና የንጉሱ ፓይለት ሄር ሉድዊግ ዌበር ብሎም በወቅቱ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ትብብር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መሰራቷ ይታወሳል። ጣልያን ኢትዮጵያ ቅኝ ለመግዛት ሁለት ጊዜ የሞከረች ቢሆንም የመጀመሪያው ሙከራ በ1880ዎቹ በኢትዮጵያዊያን አርበኞች ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ በኢትዮጵያዊያን አርበኞች የተባረረችው ጣልያን ሁለተኛውን የቅኝ ግዛት ሙከራዋን በ1927 ያደረገች ሲሆን ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ከአምስት ዓመታት ብርቱ ትግል በኋላ ድል ተቀዳጅተዋል፡፡ ጣልየን በኢትዮጵያ…