02
Aug
ጣልያናዊው ጂያንሉጂ ቡፎን ጓንቱን ሰቀለ የጣልያን ብሔራዊ ቡድን እና ጁቬንቱስ ታሪካዊ ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ቡፎን በ 45 ዓመቱ ከውድድር ራሱን እንዳገለለ አስታውቋል። ጂያንሉጂ ቡፎን በጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ቤት አስራ ሰባት አመታትን ያሳለፈ ሲሆን በክለቡ 685 ጨዋታዎች በማድረግ በክለቡ ታሪክ ብዙ ጨዋታ ያደረገ ሁለተኛው ተጨዋች ነው። ሀያ ስምንት አመታትን በተጨዋችነት ያሳለፈው የ45 ዓመቱ ጂያንሉጂ ቡፎን ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ጋር በ2006 የዓለም ዋንጫን አሸንፏል። ለጣልያን ብሔራዊ ቡድን 176 ጨዋታዎችን ያደረገው ቡፎን ለብሔራዊ ቡድኑ ብዙ ጨዋታዎችን በማድረግ ታሪካዊ ተጫዋች ነው። ተጫዋቹ ከጁቬንቱስ በተጨማሪ ወደ ፓሪስ በማቅናት በፒኤስጂ እግር ኳስ ክለብ ውስጥ ለአንድ ዓመት በግብ ጠባቂነት አገልግሏል።