Adeyabebastadium

የጣልያኑ ሊሞንታ ስፖርት ኩባንያ በኢትዮጵያ ስታዲየሞችን ለማልማት ድርድር ጀመረ

የጣልያኑ ሊሞንታ ስፖርት ኩባንያ በኢትዮጵያ ስታዲየሞችን ለማልማት ድርድር ጀመረ

በዓለም እና ስፔን እግር ኳስ ታሪክ ቀዳሚ የሆነው የሪያል ማድሪድን ስታዲየም ቤርናቢዩ ሜዳ የሰራው ግዙፍ ተቋም በአዲስ አበባ ይገኛል። ተቀማጭነቱን በጣልያን ያደረገው ሊሞንታ ስፖርት (Limonta Sport) ለስፖርት ሜዳዎች የሚሆኑ ሰው ሰራሽ (Artificial) እና ቅልቅል (Hybrid) ሳሮችን በማምረት እና በማንጠፍ ታዋቂነትን ያተረፈ የስፖርት መሰረተ ልማት ተቋም ነው። በፊፋ እውቅና ያለው ይህ ተቋም ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል። ኩባንያው በመላው ዓለም አርቴፊሻል እና ሃይብሪድ የስታዲየም ውስጥ ሳሮችን በማምረት ይታወቃል። ኩባንያው ከሚያመርታቸው የስታዲየም ውስጥ ሳር መካከል ድብልቁ ወይም ሀይብሪዱ 95 ከመቶው የተፈጥሮ ሳር ሲሆን 5 ከመቶው ደግሞ አርቲፊሻል ሴንቴቲክ ነው ። ሊሞንታ ኩባንያ የሚያነጥፈው እና የሚያበቅለው ሳሩ በዝናብ ወቅት ውሃን በ5 ደቂቃ ውስጥ የማፍሰስ ችሎታ…
Read More
አደይ አበባ ስታዲየም ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 18.6 ቢሊየን ብር ተመደበ

አደይ አበባ ስታዲየም ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 18.6 ቢሊየን ብር ተመደበ

ኢትዮጵያ የብሔራዊ ስታድየሟን ግንባታ በሁለት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዷ ተገለጸ 62 ሺህ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው አደይ አበባ ስታዲየም ግንባታው ከተጀመረ 10 ዓመት አልፎታል በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘውን አደይ አበባ ስቴዲየም ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 18 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ተገልጿል፡፡ አሁን የአደይ አበባ ስቴዲየም ቀሪ ስራዎችን ከሁለት አመት ባነሰ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ተብሏል። የስታዲየሙን የማጠናቀቂያ ሥራዎች ለማከናወን 18 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ውል መገባቱን የባህልና ስፖርት ሚንስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች አንድ ስታዲየም ያላት ቢህንም ከዚህ ውስጥ አንዱም የካፍን ደረጃ የማያሟላ ሲሆን በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው እና 62 ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው አደይ አበባ ስታዲየም ግንባታው በተለያዩ ምክንያቶች መጠናቀቅ…
Read More
ኢትዮጵያ ለአደይ አበባ ስታድየም አዲስ የግንባታ ጨረታ ልታወጣ ነው

ኢትዮጵያ ለአደይ አበባ ስታድየም አዲስ የግንባታ ጨረታ ልታወጣ ነው

ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ የቆየውን የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ በአዲሱ በጀት ዓመት እንደገና ለማስጀመር በጀት መያዙን ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ገልጿል ። የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ በ48 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባውና 62ሺ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታን ለማስቀጠል በ2016 ዓ.ም በጀት የተያዘለት በመሆኑ በቅርቡ ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቶ ግንባታው ይጀመራል። የብሔራዊ ስታዲየሙ ግንባታ በቻይናው ኩባንያ ይካሄድ እንደነበረ አስታውሰው፤ ግንባታው በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱን ገልፀዋል። በኋላም የግንባታ ተቋራጩ ለሥራው ያቀረበው የዋጋ ማስተካከያ ከገበያ በላይ የተጋነነ በመሆኑ መንግሥት ከያዘው በጀት ጋር ሊመጣጠን አልቻለም። በዚህም ከግንባታ ተቋራጩ ጋር ያለው ውል እንዲቋረጥ መደረጉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።…
Read More