16
Aug
የቻይና ሶስት ኩባንያዎች 312 ተሽከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ለመሸጥ ተስማሙ የቻይናዎቹ ዞሆንግቶን ሻንዚ እና ሻንጋይ የተሰኙ የአውቶሞቲቭ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ያወጣችውን ዓለም አቀፍ ጨረታዎችን አሸንፈዋል ተብሏል። ኢትዮጵያ ለተሽከርካሪዎቹ ግዢ 34 ሚሊዮን ዶላር በጀት መመደቧ ተገልጿል። የመንግስት ግዥ አገልግሎት በገንዘብ ሚኒስቴር ጠያቂነት ለፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች እና ለመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ጨረታ አውጥቶ ነበር። ሊገዙ የታሰቡት ተሽከርካሪዎች ብዛታቸው 312 ሲሆኑ በኤሌክትሪክና በነዳጅ የሚሰሩ እንደሆኑም ተገልጿል። ለተሽከርካሪዎች ግዢ 34 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ወጪ ይደረጋል የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 33ቱ የኤሌክትሪክ ሚኒባስ ናቸው ተብሏል። የቻይናው ዞሆንግቶን የተሰኘው ኩባንያ 47 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባሶችን በሶስት ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ ለማስረከብ ጨረታውን እንዳሸነፈ ተገልጿል።…