Tokyo2025

ኢትዮጲያ ከ34 አመት በኋላ ያለ ወርቅ ሻምፒወናዉን አጠናቀቀች

ኢትዮጲያ ከ34 አመት በኋላ ያለ ወርቅ ሻምፒወናዉን አጠናቀቀች

በጃፖን ቶኪዮ አስተናጋጅነት ሲካሄድ  የቆየዉ  የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጲያ በታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ያለ ምንም ወርቅ አጠናቃለች። ኢትዮጲያ በዚህ መድረክ በታሪክ ከ34 አመት በኅላ አንድም ወርቅ ሳታገኝ ያጠናቀቀችበት የአለም ሻምፒዮና ሆኖ ተመዝግቧል። በውድድሩ የመጨረሻ ቀናት በተደረገዉ የ5000 ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ዉድድር ምን አልባት ወርቅ ይገኝበታል ተብሎ ቢጠበቅም ኢትዮጵያ ሜዳሊያ  ዉስጥ መግባት ሳትችል ቀርታለች። ኢትዮጲያን የወከሉት አትሌት ሀጎስ ገብረ ሂወት እና አትሌት ቢኒያም መሀሪ ዉድድራቸዉን 5ኛ እና 13ኛ  ደረጃን ይዘዉ አጠናቀዋል። ኢትዮጲያ እስካሁን ባደረገቻቸዉ ስምንት የፍፃሜ ዉድድሮች ሁለት ብር እና ሁለት ነሀስ ስታገኝ በድምሩ አራት ሜዳሊያዎችን ብቻ ሰብስባ በታሪኳ በእጅጉ ደካማ የሆነዉን የቶኪዮ አለም ሻምፒዮና ቆይታዋን ደምድማለች። አሜሪካ በውድድሩ 16 የወርቅ ሜዳሊያ…
Read More