14
Aug
በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልዑክ ቡድን በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል እና የእራት ግብዣ ተደርጎለታል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በተካሄደው የአቀባበል እና የአውቅና ስነ ስርዓት ላይም ለአትሌቶች፣ አሰልጣኞች እና ለታሳታፊዎችዎች እንደየ ተሳትፏቸው እና አብርክቷቸው ከ50 ሺህ ብር እስከ 7 ሚሊየን ብር የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷል። በዚህ ስነ ስርዓት ላይ በማራቶን ለኢትዮጵያ ብቸኛውን ወርቅ ሜዳሊያ ላስገኘው አትሌት ታምራት ቶላ 7 ሚሊየን ብር እና ወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበርክቶለታል። የብር ሜዳልያ ላመጡት አትሌት ትግስት አሰፋ፣ አትሌት በሪሁን አረጋዊ እና አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለእያንዳንዳቸው የ 4 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የታምራት ቶላ እና ትግስት አሰፋ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ በስነ ስርዓቶ ላይ የ2 ሚልዮን ብር…