londonmarathon

የለንደን ማራቶን በኢትዮጵያዊያን እና ኬንያዊያን የበላይነት ተጠናቀቀ

የለንደን ማራቶን በኢትዮጵያዊያን እና ኬንያዊያን የበላይነት ተጠናቀቀ

ዛሬ ፍጻሜውን ባገኘው የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን እና ኬንያዊያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። በ2025 በሴቶች ውድድር ትግስት አሰፋ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ በወንዶች ደግሞ ኬንያዊው ሴባስቲያን አሸንፏል። አትሌት ትግስት አሰፋ በሴቶች ብቻ የአለም የማራቶን ሪከርድን ( 2:16:16 ) 2:15:50 በሆነ ሰዓት መስበር ችላለች። ታሪካዊቷ ብሪታንያዊት የማራቶን ሯጭ ፓውላ ራድክሊፍ በሰጠችው አስተያየት አትሌት ትዕግስት አሰፋ ውድድሩን የጨረሰችበትን መንገድ አድንቃ ጀግና አትሌት ነሽ ብላታለች፡፡ አትሌት ትግስት አሰፋ ውድድሯን 2:15:50 በሆነ ሰዓት በአንደኝነት ማጠናቀቋን ተከትሎ በሴቶች ብቻ የአለም የማራቶን ሪከርድን (2:16:16 ) 2:15:50 በሆነ ሰዓት መስበር ችላለች። ኬንያዊቷ አትሌት ጄፕኮስፔ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ በውድድሩ ስትጠበቅ የነበረችው ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አተናቃለች። በተመሳሳይ የወንዶች…
Read More
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ ሆነ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ ሆነ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከእሁዱ የ2025 ለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ መሆኑን አዘጋጆቹ ይፋ አድርገዋል። አትሌቲ ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት በለንደን ማራቶን ውድድር መሳተፍ እንደማይችል አስታውቋል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፌስቡክ ገጹ እንዳለው “በእሁዱ የለንደን ማራቶን ወደ ውድድር ለመመለስ ጓጉቼ ነበር ባለመሳካቱ በጣም ተበሳጭቻለሁ“ ብሏል። ከውድድሩ ውጪ የሆነው በጉዳት መሆኑን ያረጋገጠው ቀነኒሳ በውድድሩ ለሚካፈሉ አትሌቶች መልካም ምኞቱን ገልጿል። በለንደን ማራቶን ውድድር አንደኛ ሆኖ ለሚያጠናቅቅ ተወዳዳሪ 55 ሺህ ዶላር ሁለተኛ 33 ሺህ እንዲሁም ሶስተኛ ለሚወጣ ተወዳዳሪ ደግሞ 22 ሺህ ዶላር ሽልማት ያገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያዊ የረጅም ርቀት ንጉስ የሆነው ቀነኒሳ በቀለ የፊታችን እሁድ በሚደረገው የለንደን ማራቶን እንደማይሳተፍ ይፋ አድርጓል ። ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የአሜሪካው አለምአቀፍ…
Read More
ሲፋን ሀሰን የለንደን ሜራቶንን አሸነፈች

ሲፋን ሀሰን የለንደን ሜራቶንን አሸነፈች

የለንደን ማራቶች ከደቂቃዎች በፊት የሁለቱም ጾታ ተዉዳዳሪዎች ፍጻሜውን አግኝቷል። በዚህም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ እና በዜግነት ሆላንዳዊ የሆነችው ሲፋን ሀሰን አንደኛ ወጥታለች። ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን ውድድር ላይ የተሳተፈችው ሲፋን ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ37 ማይክሮ ሰከንድ አጠናቃለች። ኢትዮጵያዊቷ መገርቱ አለሙ ሁለተኛ ጀፕችርችር ፒሬዝ ከኬንያ ሶስተኛ ወጥተዋል። በርቀቱ ተጠብቃ የነበረችው አልማዝ አያና ውድድሯን በሰባተኝነት አጠናቃለች። በወንዶች የማራቶን ውድድር ደግሞ ኬንያዊው ኬልቪን ኪፕቱም በ2 ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ25 ማክሮ ሰከንድ አንደኛ ሲሆን ሌላኛው ኬንያዊ ጂዎፍሪ ካምዎሮር ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ ደግሞ ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል። ልኡል ገብረስላሴ እና ሰይፉ ቱራ ደግሞ አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ የኢትዮጵያ አትሌቶች ናቸው። በውድድሩ ተጠብቀው የነበሩት…
Read More