marathon2025

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ ሆነ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ ሆነ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከእሁዱ የ2025 ለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ መሆኑን አዘጋጆቹ ይፋ አድርገዋል። አትሌቲ ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት በለንደን ማራቶን ውድድር መሳተፍ እንደማይችል አስታውቋል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፌስቡክ ገጹ እንዳለው “በእሁዱ የለንደን ማራቶን ወደ ውድድር ለመመለስ ጓጉቼ ነበር ባለመሳካቱ በጣም ተበሳጭቻለሁ“ ብሏል። ከውድድሩ ውጪ የሆነው በጉዳት መሆኑን ያረጋገጠው ቀነኒሳ በውድድሩ ለሚካፈሉ አትሌቶች መልካም ምኞቱን ገልጿል። በለንደን ማራቶን ውድድር አንደኛ ሆኖ ለሚያጠናቅቅ ተወዳዳሪ 55 ሺህ ዶላር ሁለተኛ 33 ሺህ እንዲሁም ሶስተኛ ለሚወጣ ተወዳዳሪ ደግሞ 22 ሺህ ዶላር ሽልማት ያገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያዊ የረጅም ርቀት ንጉስ የሆነው ቀነኒሳ በቀለ የፊታችን እሁድ በሚደረገው የለንደን ማራቶን እንደማይሳተፍ ይፋ አድርጓል ። ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የአሜሪካው አለምአቀፍ…
Read More