19
Nov
በበርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ስኬታማ አትሌት የሆነው ሀይሌ ገብረስላሴ የሮጠበት አንድ ማልያ በ2 ሺህ 400 ዶላር ተሸጧል፡፡ በአዲስ አበባ በተካሄደ በዚህ ጨረታ ላይ የቀረበው ይህ ማልያ አትሌት ሀይሌ በ1992 በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ በተካሄደው የ10 ሺህ ሜትር ውድድርን ያሸነፈበት ማልያ ነበር፡፡ ይህ ውድድር ለአትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የጀመረበት ወቅት እንደነበርም ተገልጿል፡፡ የታላቁ ሩጫ መስራች እና ባለቤት አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ለጨረታ ቀርቦ 2 ሺሕ 400 ዶላር የተሸጠው ማልያ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለማጠናከር ይውላልም ተብሏል፡፡ በጨረታው የታላቁ ሩጫ ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ፕሮግራም ላይ የኃይሌ ገ/ሥላሴ የሮጠበት ማልያ፤ በእንግሊዛዊ ተጋባዥ እንግዳ አሸንፏል። ይህንን የማልያ ጨረታ እንግሊዛዊ ዜግነት ያለው…