Egypt

የግብፅ ወታደሮች ሶማሊያ መግባታቸው ተገለጸ

የግብፅ ወታደሮች ሶማሊያ መግባታቸው ተገለጸ

የግብፅ ወታደሮች፣ መሳሪያዎችና ወታደራዊ አውሮፕላኖችን የያዘ አውሮፕላን ወደ ሶማሊያ መጓዛቸውን የሚያሳይ ምስሎች ወጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ከዘጠኝ ወር በፊት በአዲስ አበባ የወደብ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ስምምነትን ተከትሎ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው የተበላሸ ሲሆን ሶማሊያ ከግብጽ እና ቱርክ ጋር ወታደራዊ ስምምነቶችን አድርጋለች፡፡ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በአፍሪካ ትልቁን ግድብ ግንባታ መጀመሯን ተከትሎ የውሃ ድርሻዬ ነካል በሚል ቅሬታ ያላት ግብጽ ይህንን እድል በመጠቀም ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነቶችን እያደረገች ነው፡፡ ይህን ተከትሎም ግብጽ ከሶማሊያ ጋር ባደረገቻቸው ወታደራዊ ስምምነቶች አማካኝነት በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ሞቃዲሾ ልካለች፡፡ ን የተፈራረምክንያት ይህ ሂደት 10 ሺህ የሚደርሱ የግብፅ ወታደሮችን በሶማሊያ ለማሰማራት የታቀደው…
Read More
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ብሔራዊ ጥቅሟል ለማስጠበቅ ማንኛውንም እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ገለጸች

ኢትዮጵያ በሶማሊያ ብሔራዊ ጥቅሟል ለማስጠበቅ ማንኛውንም እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ገለጸች

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ወቅት ከጋዜጠኞች ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል የግብጽ እና ሶማሊያ ወታደራዊ ስምምነቶች በኢትዮጵያ ላይ ምን አይነት አንድምታ ይኖረዋል? የሚለው ዋነኛው ነበር። እንዲሁም የሶማሊያን ጸጥታ እና ደህንነት ለማስጠበቅ በሚል በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የተሰማራው ሰላም አስከባሪ ጦር (አትሚስ) ተልዕኮ የፊታችን ታህሳስ ያልቃል። የሶማሊያ ጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት አሁንም የሚፈለገውን አቅም አለመገንባታቸውን ተከትሎ አትሚስን ተክቶ እንደ አዲስ በሚዋቀረው ሰላም አስከባሪ ስር ግብጽ ጦር ለማዋጣት ፍላጎት ማሳየቷ እና የሶማሊያ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጦር በአዲሱ ተልዕኮ ስር እንዳይካተት መፈለጋቸውስ በኢትዮጵያ ላይ ምን አይነት አስተዋጽኦ ይኖረዋል? የሚለው ጥያቄም ለአምባሳደር ነብዩ ተነስቶላቸዋል።…
Read More
አሜሪካዊው ፖለቲከኛ ቦብ ሜንድዝ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋገጠ

አሜሪካዊው ፖለቲከኛ ቦብ ሜንድዝ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋገጠ

ቦብ ሜንድዝ ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ የሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡ የዘር ሀረጋቸው ከኩባ የሚመዘዘው ሜንድዝ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤትን ከመቀላቀላቸው በፊት የኒው ጀርሲዋን ዩኒየን ሲቲን በከንቲባነት አገልግለዋል፡፡ እኝህ ጉምቱ ፖለቲከኛ በፈረንጆቹ 2020 ላይ የወቅቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አድርገዋል ተብሏል፡፡ እንደ አሜሪካ ድምጽ ዘገባ ከሆነ ፖለቲከኛው ይህን ያደረጉት ከግብጽ ባለስልጣናት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ጉቦ ከተቀበሉ በኋላ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ…
Read More
ሶስተኛው የህዳሴው ግድብ ድርድር በካይሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ሶስተኛው የህዳሴው ግድብ ድርድር በካይሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ በሱዳን ለተከሰተው ጦርነት እልባት ለመፈለግ በሚል በካይሮ በተካሄደው የጎረቤት ሀገራት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድርን ለማስቀጠል መስማማታቸው ተገልጾ ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረት ከሶስት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የግድቡ ተደራዳሪ የቴክኒክ ባለሙያዎች በግብጽ ካይሮ ተገናኝተው ተወያይተዋል። እንዲሁም ሁለተኛው ዙር የቴክኒክ ባለሙያዎች ውይይት ደግሞ ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የግድቡ ተደራዳሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ዲፕሎማቶች የተሳተፉበት ይህ ውይይት ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱም ሀገራት በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ የግብጽ ውሃ እና መስኖ ሚኒስትር ሀኒ ስዌለም እንዳሉት በአዲስ አበባ የተካሄደው ድርድር…
Read More
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የሶስትዮሽ ድርድር በአዲስ አበባ ተጀመረ

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የሶስትዮሽ ድርድር በአዲስ አበባ ተጀመረ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ ግብጽ በሱዳን መረጋጋት ዙሪያ ባዘጋጀችው የጎረቤት ሀገራት የመሪዎች መድረክ ላይ በተገኙበት ወቅት ከግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር በግድቡ ዙሪያ መምከራቸው ይታወሳል፡፡ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ መወያየታቸው ሲገለጽ የግድቡ ውሀ አሞላል ዙሪያ ተወያይተው እስከ መስከረም ወር ድረስ ተቋርጦ የነበረውን የሶስትዮሽ ውይይት ለማስጀመር ተስማምተው ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረት ከሁለት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የግድቡ ተደራዳሪ የቴክኒክ ባለሙያዎች በግብጽ ካይሮ ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡ ሁለተኛው የሶስትዮሽ ውይይትም ዛሬ በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የግድቡ ተደራዳሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት በሁለት ተርባይኖቹ ሀይል ማመንጨት የጀመረው የሕዳሴው ግድብ…
Read More
አዲስ አበባ ቀጣዩን የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር እንድታካሂድ ተመረጠች

አዲስ አበባ ቀጣዩን የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር እንድታካሂድ ተመረጠች

የህዳሴው ግድብ የቴክኒክ ባለሙያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ባለፉት ሁለት ቀናት በግብጽ ካይሮ መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪው አባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተለያዩ ምክንያቶች መቋረጡ ይታወሳል። ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የሶስትዮሽ ድርድር  ሲያካሂዱ ቆይተዋል። በሱዳን እና በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት ለሶስትዮሽ ድርድር አለመቀጠል እና የግብጽ ተለዋዋጭ አቋም ማሳየት ለድርድሩ አለመሳካት ዋነኞቹ ምክንያቶች ነበሩ። ከአንድ ወር በፊት በግብጽ ካይሮ በሱዳን ለተከሰተው ጦርነት እልባት ለመፈለግ በሚል በተካሄደው የጎረቤት ሀገራት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እግረ መንገዳቸውን ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ  አልሲሲ ጋር መክረዋል። ሁለቱ መሪዎች ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከልም…
Read More
የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በግብጽ ተጀመረ

የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በግብጽ ተጀመረ

ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪው አባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተለያዩ ምክንያቶች መቋረጡ ይታወሳል። በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ሲካሄድ የቆየው ይህ የሶስትዮሽ ድርድር በኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳን መካከል ሲካሄድ ቆይቷል። በሱዳን እና በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት ለሶስትዮሽ ድርድር አለመቀጠል እና የግብጽ ተለዋዋጭ አቋም ማሳየት ለድርድሩ አለመሳካት ዋነኞቹ ምክንያቶች ነበሩ። ከአንድ ወር በፊት በግብጽ ካይሮ በሱዳን ለተከሰተውን ጦርነት እልባት ለመፈለግ በሚል በተካሄደው የጎረቤት ሀገራት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እግረ መንገዳቸውን ከፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር መክረዋል። ሁለቱ መሪዎች ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከልም የህዳሴው ግድብ ጉዳይ ዋነኛው ሲሆን በሶስት ወራት ውስጥ ዳግም ድርድር…
Read More
ሩሲያ ለአፍሪካ ገበያ በግብጽ የላዳ መኪና ፋብሪካ ልትገነባ መሆኗን ገለጸች

ሩሲያ ለአፍሪካ ገበያ በግብጽ የላዳ መኪና ፋብሪካ ልትገነባ መሆኗን ገለጸች

የሩሲያ ምርት የሆነው ላዳ መኪና በኢትዮጵያ እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተመራጭ ነበሩ። ለዓመታት ገበያውን ተቆጣጥረውት የቆዩት የሩሲያ ላዳ መኪኖች ቀስ በቀስ ከዓለም እና አፍሪካ ገበያዎች እየጠፉ መጥተዋል። ኩባንያው ምርቶቹን ወደ አፍሪካ ገበያዎች ማቅረብ ያቆመው ከቀዝቃዛው ጦርነት ጋር በተያያዘ የሩሲያ ተጽዕኖ እየቀነሰ በመምጣቱ እና በገበያ ውድድር ምክንያት እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል። ሩሲያ ወደ አፍሪካ ገበያዎች ዳግም የመመለስ ፍላጎት ማሳየቷን ተከትሎ ኩባንያው ከወራት በፊት በኢትዮጵያ እና ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ምቹ ሁኔታዎችን ተመልክቶ ተመልሷል። የኩባንያው ሀላፊዎች በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገውም ነበር። ይሁንና በፒተርስግበርግ ከየማ እየተካሄደ ባለው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ መካሄዱን ተከትሎ ኩባንያው ዋና ሙቀመጫውን ግብጽ ለማድረግ መወሰኑን…
Read More
ኢትዮጵያ እና ግብጽ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ በአራት ወራት ውስጥ ችግራቸውን ለመፍታት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ግብጽ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ በአራት ወራት ውስጥ ችግራቸውን ለመፍታት ተስማሙ

ግብጽ በሱዳን ያለውን ጦርነት ለማስቆም ያለመ ውይይት የጎረቤት ሀገራት መሪዎችን መጋበዟ ይታወሳል። ኢትዮጵያን ጨምሮ የሱዳን ጎረቤት ሀገራት በመድረኩ ላይ ለመሳተፍ ወደ ካይሮ ያመሩ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከውይይቱ በተጓዳኝ ከፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር መወያየታቸው ተገልጿል። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ መወያየታቸው ሲገለጽ የግድቡ ውሀ አሞላል ደግሞ የመሪዎቹ ዋነኛ መወያያ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ በግድቡ ውሀ አሞላል ዙሪያ ግብጽን እና ሱዳንን የመጉዳት ፍላጎት የላትም የተባለ ሲሆን በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ተጨማሪ ውይይቶችን ለማድረግ ስለመስማማታቸውም ተገልጿል። ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳንም በህዳሴው ግድብ ውሀ አሞላል እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያለባቸውን አለመግባባት በአራት ወራት ውስጥ በሚያደርጉት ውይይት ወደ…
Read More
ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ውሀ መያዣ ጊዜን አራዘመች

ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ውሀ መያዣ ጊዜን አራዘመች

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እስከ መስከረም ውሀ እንደማይዝ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተናግረዋል። ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ እየሰጡ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ከአባላቱ ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ ውሀ ሙሌት አይከናወንም ብለዋል። "ኢትዮጵያ የሱዳንን እና ግብፅ ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ የህዳሴ ግድብ ሙሌቱ እስከ መስከረም መጀመሪያ አታከናውንም" ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከሀምሌ ወር ጀምር ውሀ ሲይዝ የቆየ ሲሆን ዘንድሮ ግን ውሀ የመያዣው ጊዜ ወደ መስከረም መዛወሩ ተገልጿል። እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ገለጻ የዘንድሮው ውሀ ሙሌት ወደ ግብጽ እና ሱዳን በቂ የዉሃ ከደረሰ በኋላ ሙሌቱ…
Read More