Itsmydam

ኢትዮጵያ ግብጽን በስጋትነት እንደማትመለከታት ገለጸች

ኢትዮጵያ ግብጽን በስጋትነት እንደማትመለከታት ገለጸች

ግብፅ ህዳሴ ግድቡን በተመለከተ እያደረገች ያለችውን ጫና ኢትዮጵያ በስጋት አንደማትመለከተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ሳምንታዊ መግለጫ ግብፅ የታላቁ ህዳሴ ግድቡን በተመለከተ የዲፕሎማሲ ጫና ለመፍጠር የምታደርገው ጥረት ለኢትዮጵያ ስጋት አይሆንም ሲል ተናግሯል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር  ነቢያት ጌታቸው የግብፅ አካሄድ ስጋት የማይሆነው ከዚህ ቀደምም የነበረ ስለሆነ ነው ብለዋል። የህዳሴ ግድቡ ምርቃት መቃረቡን ያስታወሱት አምባሳደር  ነቢያት ጌታቸው የቅኝ ግዛት እሳቤዎች ተቀባይነት የላቸውም ብለዋል። በለፉት 14 ዓመታት በመላው ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ ከፍተኛ መሰናክሎችን አልፎ ህዳሴ ግድቡ የመመረቅያው ዋዜማ ላይ እንገኛለን ያሉት አምባሳደሩ ምርቃቱንም ኢትዮጵያዊያን  እና የኢትዮጵያን በጎ የሚመኙ አብረውን የሚያከብሩት  ይሆናል ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ለምርቃቱ በስም ያልዘረዘሯቸው እንግዶች እንደተጋበዙ…
Read More