03
Apr
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ ታሪፍ እንዲጣል ያዘዙ ሲሆን ኢትዮጵያም ወደ አሜሪካ በምትልካቸው ምርቶች ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ተጥሎባታል። ፕሬዚዳንቱ በነጩ ቤተ መንግሥት በሰጡት መግለጫ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ አዲስ የታሪፍ መጠኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል። እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ እርምጃው አሜሪካን ቀዳሚ ለማድረግ እና የንግድ ጉድለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። በአብዛኛዎቹ ሀገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ10% እስከ 49% የሚደርስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም 10% ታሪፍ ተጥሎባታል። ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከተሞች አበባ፣ ቡና፣ የቆዳ እና አልባሳት ምርቶችን በመላክ ላይ ስትሆን ተጨማሪ 10 በመቶ ቀረጥ ለመክፈል ትገደዳለች። አሜሪካ የንግድ ጉድለቷን ለመቀነስ እና የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ ይህን እርምጃ እንደወሰደች የገለፁት…