Binalfandualem

አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም በፕሬዝዳንት ትራምፕ አቀባበል ተደረገላቸው

አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም በፕሬዝዳንት ትራምፕ አቀባበል ተደረገላቸው

አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተ-መንግሥት ተገናኝተው ተወያይተዋል ። በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተ-መንግሥት ተገናኝተው ተወያይተዋል። አምባሳደር ብናልፍ ነጩ ቤተ-መንግሥት ሲደርሱ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚያንጸባርቅ ዲፕሎማሲያዊ አቀባበል እንደተደረገላቸው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ይህ የመጀመሪያ ግንኙነት በቀጣይ ጊዜያት ለሚደረጉ ውይይቶች መጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል የተባለም ሲሆን፤ አምባሳደሩ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ተገናኝተው ስላደረጉት ውይይት በይፋ የተገለጸ ነገር የለም ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ በሁለቱ አገራት መካከል እንደ ሰላም፣ ጸጥታና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ጠንካራ አጋርነት ከመፍጠር አንጻር ያሉ ዕድሎችም ሰፊ…
Read More