Nilerights

ኢትዮጵያ በግብፅ ለተስተጓጎሉ ፕሮጀክቶች ካሳ ልትጠይቅ ነው

ኢትዮጵያ በግብፅ ለተስተጓጎሉ ፕሮጀክቶች ካሳ ልትጠይቅ ነው

ኢትዮጵያ በግብፅ ምክንያት የተስተጓጎሉ ወይም የተከለከሉ የውሃ ልማት ፕሮጀክቶች ያደረሱትን የኢኮኖሚ ጉዳት እና ያመለጡ የልማት ዕድሎችን የሚያጠና ብሔራዊ ኮሚቴ ማቋቋሟን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) አስታወቁ።ሚኒስትሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ እንዳስታወቁት፣ ኮሚቴው እስካሁን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በግብፅ ምክንያት ተፅዕኖ የወደቀባቸውን ከ22 በላይ የልማት ፕሮጀክቶችን ለይቷል።አዲሱ ኮሚቴ ማስረጃዎችን በማቀናጀት ኢትዮጵያ ልትጠይቅ የምትችለውን የካሳ መጠን መሰረት በመመርመር ላይ ይገኛል። በጥናት እና ግምገማ ሂደቱም ባለሙያዎች፣ የቀድሞ ሚኒስትሮች፣ አማካሪዎች እና የህግ ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ እንደሆኑ ተገልጿል።ሀብታሙ እንደገለጹት ግብፅ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ በበርካታ ፕሮጀክቶች ላይ ተቃውሞና ወታደራዊ ዛቻ በማቅረብ የፈጸመችውን ተግባር ኮሚቴው በማስረጃነት እያሰባሰበ ይገኛል።ጥናቱ ተግባራዊ እንዳይሆኑ የተከለከሉ ፕሮጀክቶችን ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ…
Read More