EthioNegari

ደረሰኝ የማይሰጡ ነጋዴዎች የ100 ሺህ ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተባለ

ደረሰኝ የማይሰጡ ነጋዴዎች የ100 ሺህ ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተባለ

በግብይት ወቅት ማናቸውም ግብር ከፋይ ነጋዴ ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲያከናውን ወይም ዋጋ አሳንሶ የተገኘ በእያንዳንዱ ደረሰኝ የአንድ መቶ ሺህ ብር ቅጣት መጣል የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። ያለ ደረሰኝ ሲገበያይ የተገኘ ማንኛውም ግብር ከፋይ ለገዢ ባልሰጠው በእያንዳንዱ ደረሰኝ ብዛት ከዚህ ቀደም 50 ሺህ ብር ይቀጣ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ማሻሻያ በተደረገለት የታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ መሰረት ወደ አንድ መቶ ሺህ ብር ቅጣት ከፍ ብሏል።የገንዘብ ሚኒስቴር እንደ ዋና ማሻሻያዎች ካነሳቸው መካከል የታክስ የምስክር ወረቀት አሰጣጥን ማሻሻል፣ የታክስ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ በማስታረቅ ሥርዓት መፍታት፣ የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ የሚታረምበትን ሥርዓት ግልጽ ማድረግ፣ እንዲሁም የውሳኔ ማስታወቂያ ማሻሻያና የይግባኝ ማቅረቢያ የጊዜ ገደቦችን በግልጽ ማስቀመጥ የሚሉት ይገኙበታል።እነዚህ…
Read More
ኢትዮጵያ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ዜጎቿ ደህንነት እንዲጠበቅ መጠየቋ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ዜጎቿ ደህንነት እንዲጠበቅ መጠየቋ ተገለጸ

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ መጠየቃቸው ተገልጿል። ሚንስትሩ ጌዲዮን ይህን ጥያቄ ያቀረቡት፣ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከሳዑዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋሊድ ኤልክረጂ ጋር በተወያዩበት ወቅት መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባሠራጨው መረጃ ገልጧል። ጌዲዮን፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ለኢትዮጵያዊያን ሠራተኞች ሕጋዊ የሥራ እድሎችን እንዲያመቻችም መጠየቃቸውን ሚንስቴሩ ጠቅሷል። ሚንስትር ዋሊድ፣ ሕጋዊ የሠራተኞች ፍልሠት ኢትዮጵያዊያን ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ቅጥር እድል እንዲያገኙ ለማስቻል አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ተብሏል። የሳዑዲ ዓረቢያ ፍርድ ቤት ከአደንዛዥ እጽ ዝውውር ጋር በተያያዘ የሞት ቅጣት የጣለባቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በውይይቱ ወቅት ይነሳ አይነሳ መረጃው አላመለከትም። በየ ዓመቱ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ…
Read More
ባለፉት 10 ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 8.7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

ባለፉት 10 ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 8.7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት በ10 ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ  8.71 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር አስታውቋል። በ2018 በጀት ዓመት የ10 ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከታቀደው ግብ በላይ ውጤት መመዝገቡን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል። ሚኒስትሩ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ 10 ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 7.25 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ፣ 8.71 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን አስታውቀዋል። የወጪ ንግድ አፈጻጸም ባለፈው ዓመት (2017 ዓ.ም) ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው የ6.08 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ43.32 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንም ሚንስትሩ አብራርተዋል። ይህ ስኬት በዋናነት በንግድ ዘርፉ ላይ የተወሰዱ የፖሊሲ እርምጃዎች ውጤት መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመው፤ በላኪዎችና በዘርፉ ተዋንያን መካከል የተፈጠረው…
Read More
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ አነሳች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ አነሳች

በኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መነሳቱን አሜሪካ አስታውቃለች። ማዕቀቡ መነሳቱን የገለፀው በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገር መከላከያ ንግድ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ነው። ዳይሬክቶሬቱ፣ በኢትዮጵያ ላይ ይከተል የነበረውን የክልከላ ፖሊሲ በማንሳት አሁን ላይ በዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ ዝውውር ደንብ (ITAR) ቁጥጥር የሚደረግባቸውን እና ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዙ የፈቃድ ማመልከቻዎችን በየተራ እየገመገመ ነው። ይህን ተከትሎ በቅርቡ በሚወጣ የደንብ ለውጥ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ዝውውር ደንብ - ITAR 126.1 ዝርዝር ውስጥ ከሚገኙ አገራት ተርታ "እንድትሰረዝ" የሚደረግ መሆኑን ጠቅሷል። ይህ ደንብ በአሜሪካ ማዕቀብ ስር የሚገኙ የተወሰኑ አገራት፤ ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለፖሊስ፣ ለደህንነት እና ለሌሎችም የአገር ውስጥ የጸጥታ ኃይሎቻቸው የሚሆኑ የመከላከያ ቁሳቁሶችን እና አገልግሎቶችን ከውጭ…
Read More
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሙስና ምክንያት 16 ሰራተኞችን ከስራ አሰናበተ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሙስና ምክንያት 16 ሰራተኞችን ከስራ አሰናበተ

ተቋሙ የስነ ምግባር ጥሰት ፈጽመዋል ያላቸውን 1 ሺህ 139 ሠራተኞች ላይ እርምጃመውሰዱን አስታውቋል።  እርምጃ ከተወሰደባቸው ኃላፊዎችና ሠራተኞች መካከል 16 ሲሰናበቱ፤ 721 የደሞዝ ቅጣት የተቀጡ እንዲሁም 402 የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ናቸው፡፡ አገልግሎቱ በ1 ሺህ 139 ሠራተኞች ላይ ከወሰዳቸው አስተዳደራዊ እርምጃዎች መካከል 103 ሠራተኞች ላይ በደንበኞች የቀረበን ጥቆማ በመመርመር የወሰደው ሲሆን ቀሪ 1 ሺህ 36ቱ ተቋሙ በራሱ ግኝት አጣርቶ የወሰዳቸው እርምጃዎች ናቸው፡፡ ባለፉት ዘጠኝ ወራት አገልግሎቱ በሙስና መጠቆሚያ ዘመናዊ መተግበሪያ (Corruption Reporting App) እና በሌሎች አማራጮች ከደንበኞቹ የደረሱትን 427 ጥቆማዎችን መርምሮ በ103 ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስጃለሁ ብሏል፡፡   በደንበኞቹ በቀረቡት ጥቆማዎች መሰረት 14 የፅሁፍ፣ 80 የደሞዝ ቅጣት፣ 2 ከቦታ የማንሳትና 7 ስንብት በድምሩ 103…
Read More
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ወራት ውስጥ ከኪሳራ ወደ ትርፍ እንደሚሸጋገር አስታወቀ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ወራት ውስጥ ከኪሳራ ወደ ትርፍ እንደሚሸጋገር አስታወቀ

ከአምስት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ማድረጉን ገልጿል። ለኢንቨስትመንት ያወጣውን ወጪ ሳይመልስ የቆየው ኩባንያው ኪሳራው እየቀነሰ መምጣቱን ገልጾ በቀጣዮቹ ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትርፍ እንደሚገባ አስታውቋል። መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ130 በመቶ ብለጫ አንዳለው የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄሌፑት ገልጸዋል፡፡ በጊዜው ኩባንያው 39.5 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወይም 47.7 ቢሊዮን ብር አካከባቢ ኪሳራ አስመዝግቧል፡፡ ኪሳራው አምና በተመሳሳይ ጊዜ ከተመዘገበው በግማሽ ያህል መቀነሱንም ዋና ስራ አስፈጻሚው ጠቅሰዋል፡፡ ኩባንያው በዓመቱ ውስጥ ካገኘው 15.9 ቢሊዮን ብር ውስጥ 9.6…
Read More
ኢትዮጵያ በሱዳን የተነሳትን ክስ ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ በሱዳን የተነሳትን ክስ ውድቅ አደረገች

ከሰሞኑ በጀነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ከባህርዳር የተነሱ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ካርቱም ኤርፖርት ላይ ጥቃት አድርሰዋል የሚል ክስ አቅርቦ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና መከላከያ ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ህዝቦች ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት አንዳንድ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት በመጣስ የሚያደርጉትን ትንኮሳ ለህዝብ ይፋ ከማድረግ መቆጠቡን አንስቷል፡፡ የሱዳን ጦር የህወሃት ቅጥረኛ ወታደሮችን በእርስ በርስ ጦርነቱ ውስጥ ማሳተፉን እና ለእነዚህ ቅጥረኛ ወታደሮች  የጦር መሳሪያ እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በምዕራብ ኢትዮጵያ ትንኮሳ እንዲፈፅሙ ማድረጉን በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት…
Read More
በደቡብ አፍሪካ ሰባት ኢትዮጵያዊያን መገደላቸው ተገለጸ

በደቡብ አፍሪካ ሰባት ኢትዮጵያዊያን መገደላቸው ተገለጸ

‎በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ ባጋጠመው ቀውስ ምክንያት መጎዳታቸውን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በደርባን አከባቢ' ማርች ቱ ማርች ' በተባለ ስደተኛ ጠል አማጺ ቡድን ተደጋጋሚ ጥቃቶች በአጠቃላይ ስደተኞች ላይ ይፈፀሙ እንደነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በጁሀንስበርግ አካባቢ በኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ተደጋጋሚ ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።‎‎ካሳለፍነው መጋቢት ወር አጋማሽ ጀምሮ በተከታታይ ቀናት 2 ለረጅም ዓመታት በሀገሪቱ የኖሩና ሃብት ያፈሩ አቶ ወንድሜነህ አየለ እና አብረሃም ይመር የተባሉ ኢትዮጵያውያን በጁሀንስበርግ ጂፒ ስትሬት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በ16 እና በ3 ጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተገልጿል።‎‎በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያኑ አክለውም " ሁለቱም ግለሰቦች የኢትዮጵያውያን አስተባባሪና በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካም ትልልቅ ፎቆች ያሏቸው የተከበሩ ባለሃብቶች ነበሩ " ብለዋል።…
Read More
ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ ሰዎች እስከ አንድ ሚሊዮን ብር እንዲያሲዙ የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጀ

ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ ሰዎች እስከ አንድ ሚሊዮን ብር እንዲያሲዙ የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጀ

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ወደ ውጭ አገር ሄደው ለሚታከሙ ዜጎች ጥራት ያለው፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ክብራቸውን የሚመጥን የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ያለውን "የውጭ አገር የሕክምና አገልግሎት ቅብብሎሽ ሥርዓት ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 1128/2018" አውጥቷል። ይህ አዲስ መመሪያ በዋነኝነት የታካሚዎችን እንግልት ለመቀነስ፣ የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችን ለመሙላት እና በሕክምና ስም የሚከናወኑ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር ታስቦ የተዘጋጀ  መሆኑን አስታውቋል። መመሪያው በጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2017 መሰረት የወጣ ሲሆን፣ ከሕክምና ቦርድ አሰራር ጀምሮ እስከ ወኪል ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ድረስ ያሉ ሂደቶችን በዝርዝር ይደነግጋል። በመመሪያው መሰረት አንድ ታካሚ ወደ ውጭ አገር ሄዶ እንዲታከም የሚፈቀድለት አራት ዋና ዋና መስፈርቶችን ሲሟሉ እንደሆነ ያስገድዳል። ከመስፈርቶች መካከልም የሚፈለገው የሕክምና ዓይነት…
Read More
ምርጫ ቦርድ 22 ምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን ገለጸ

ምርጫ ቦርድ 22 ምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን ገለጸ

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮችን ምዝገባ እንዲያከናውኑ ከተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች መካከል 22ቱ ህገወጥ ድርጊት በመፈጸማቸው ምክንያት መዘጋታቸውን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ለ45 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁን አስመልክቶ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ሀይሉ በሰጡት መግለጫ የመራጮች ምዝገባ 50 ሚሊዮን ማለፉን ተናግረዋል፡፡ የተዘጉት የምርጫ ጣቢያዎች ተመሳሳይ መራጭ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያ ላይ ተመሳሳይ ፊርማ የተገኙባቸውም አሉ ብሏል።  ቦርዱ መስራት የሚጠበቅባቸውን ስራ ወደ ጎን በመተው ህግን ያላከበረ አሰራር መከተላቸውንም አመልክቷል። በተመሳሳይ እንዲህ ዓይነት ድርጊት ላይ የተሳተፉ የምርጫ አስፈፃሚዎችም ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል። ቦርዱ እርምጃ እንደወሰደ ቢገልጽም በምን ያህሎቹ ላይ እንደወሰደ ግን ያለው ነገር የለም።  ቦርዱ ከዚህ ቀደም በደመወዝ እና በተለያዩ ጉዳዮች…
Read More