Forcedconscription

በትግራይ ክልል ታዳጊዎች በሀይል ለውትድርና እየተመለመሉ መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ

በትግራይ ክልል ታዳጊዎች በሀይል ለውትድርና እየተመለመሉ መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እንዳስታወቀው ከሰኔ 17 ቀን 2018 ጀምሮ ደግሞ የግዳጅ ውትድርና ህግ ወጥቶለት ስራ ላይ መዋሉን ገልጿል። ይህ አዋጅ የዜጎችን ሰብአዊ መብቶችን የሚጥስ በመሆኑ እንዲቆም ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡ በትግራይ ክልል የግዳጅ ውትድርና ሰነድ ከመውጣቱ  አስቀድሞ በተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶችን በተለይም ሕጻናትን፣ ተፈናቃዮችን፣ የአእምሮ ጤና ሕሙማንን፣ እንዲሁም ከስደተኛ ካምፖችና ከጸበል ሥፍራዎች ጭምር በግዳጅ በማሰባሰብ ወደ ወታደራዊ ሥልጠና ካምፖች የማስገባት ተግባር ሲፈጸም እንደነበር ኢሰመኮ ተናግሯል፡፡ ኮሚሽኑ የግዳጅ ውትድርና ሰነዱ ከወጣ በኋላም ይህ ተግባር ይበልጥ ተጠናክሮ ቀጥሎ የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ከአብያተ ክርስትያናት፣ እንዲሁም በርካታ ሌሎች ሰዎችን ከገበያ ስፍራ፣ ከወጣቶች ማዘውተሪያ ማዕከላት እና ቤት ለቤት በሚደረግ አሰሳ በማፈስ ወደ ወታደራዊ ተግባር እንዲሰማሩ መደረጉን…
Read More