የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ

መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት 80 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት፣ የተገኘው ትርፍ ባንኩ ባለፉት ጊዜያት ካጋጥሙት የህልውና አደጋ መውጣቱን ያሳያል ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ባንኩ ከስድስት ዓመታት በፊት ከነበረበት ችግር ወጥቶ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ደረጃ ቀዳሚ ከሚባሉ ጠንካራ ባንኮች ተርታ መሰለፉንም ተናግረዋል።

ባንኩ ለደረሰበት ከፍተኛ የትርፍ መጠን በዋናነት ለግል ዘርፉ የሰጠው ትኩረት፣ የተበላሸ ብድር መጠን መቀነሱ እና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት መስፋፋትን በምክንያትነት አንስተዋል።

ባንኩ እየተጠናቀቀ ባለው የዘንድሮው በጀት ዓመት 648 ቢሊዮን ብር አዲስ ብድር እንደሰጠም ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል።

ከተሰጠው ብድር ውስጥም 90 በመቶ የሚሆነውን ወይም 588 ቢሊዮን ብር ለግል ዘርፍ መቅረቡም ተገልጿል።

ባንኩ በተጨማሪም ከ707 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰቡ ሲገለጽ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ ደግሞ ከ2 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።

ባንኩ በቀጣዩ በጀት ዓመት 832 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ለመሰባሰብ ማቀዱን ሲገልጽ እንዲሁም አጠቃላይ አመታዊ ገቢውን ደግሞ 360 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ማቀዱ ተሰምቷል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *