18
Jun
ዓለም ባንክ ከአንድ ወር በኋላ ለኢትዮጵያ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በጀት ድጋፍ ሊያጸድቅ መሆኑን ገልጿል። አንድ የባንኩ ከፍተኛ ባለሙያ ሲናገሩ አዲስ ማለዳ ሰምታለች። የገንዘብ ሚኒስቴር ከሳምንት በፊት የ2019 ዓ.ም የበጀት ረቂቀን ለምክር ቤቱ ባቀረበበት ወቅት ከ2.3 ትሪሊዮን ብር በላይ መሆኑን ገልፆ የበጀት ጉድለቱ ከውጭ እርዳታ እና ሀገር ውስጥ በሚገኝባቸው ገቢ ይሸፈናል ማለቱ ይታወሳል። በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ቢሮ የግሉ ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብስራት ተሾመ እንደገለጹት ከሆነ ባንኩ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚውል የአንድ ጊዜ የበጀት ድጋፍ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። ባለሙያው ይህን ያሉት ትናንት ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር ባዘጋጁት የውይይት መድረክ…