UNECA

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አለም አቀፍ ሹመት አገኙ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አለም አቀፍ ሹመት አገኙ

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት እና አንጋፋ ዲፕሎማት የሆኑት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  አዲስ ሹመት ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡ ሹመቱን የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ እንደሰጡ ቢሮው በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል። ፕሬዝደንቷ የተመደቡት በምእራብ አፍሪካና ሳህል ቢሮ ውስጥ ገለልተኛ ስትራቴጂያዊ ግምገማ እንዲያደርጉ ሲሆን፣ ዋና ተግባራቸውም ተቋሙ ለአካባቢው ቀውሶች በሚሰጠው ዘገምተኛ ምላሽ ሳቢያ የሚነሱበትን ትችቶችና የአሰራር ክፍተቶችን መመርመር ነው።ወይዘሮ ሳህለወርቅ ከሀምሌ ወር ጀምሮ አዲሱን ሹመት ተቀብለው ስራ እንደሚጀምሩ ተገልጿል፡፡ ወይዘሮ ሳህለወርቅ ስራቸውን ከመጀመራቸው በፊት በመጀመሪያ ወደ ኒውዮርክ በማቅናት ከፀጥታው ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ይቀበላሉ የተባለ ሲሆን፣ በመቀጠልም የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ወደሚገኝበት ሴኔጋል ዳካር በመጓዝ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ይወያያሉ።ለቀድሞዋ ፕሬዝደንት ይህ…
Read More