16
Jun
“ጁንቱ ቴክኖሎጂስ ግሩፕ” የ“ቼሪ” አውቶሞቢል ኩባንያ (Chery Automobile) ምርቶችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ “ኦሞዳ” (OMODA E5) እና “ጃይኮ” (JAECOO J5) የተሰኙትንና የ“ቼሪ” ምርቶች የሆኑትን ሁለት የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎችን ለኢትዮጵያ ገበያ በማቅረብ የዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ወኪል አቅራቢነቱን ማስፋፋቱን ገልጿል፡፡ ድርጅቱ ስራውን በዓለም አቀፍ ደረጃ በታወቀ አገልግሎት፣ በላቀ ቴክኖሎጂ እና በረጅም ጊዜ የገበያ ኢንቨስትመንት ለመምራትም “የጁንቱ-ኦሞዳ-ጃይኮ” የምርት ማሳያ (ሾውሩም) እና የድህረ ሽያጭ አገልግሎት ማዕከሉን ሰሞኑን ስራ አስጀምሯል። የጁንቱ ቴክኖሎጂስ ትሬዲንግ የኦሞዳ እና ጃይኮ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክንዴ መቻል፣ ጁንቱ ቴክኖሎጂስ ከሁለት ወራት በፊት አራት ዓይነት የ“ጂ.ኤ.ሲ” (GAC) የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎችን ለገበያ ማቅረቡን አስታውሰው፣ በቅርቡ ደግሞ “ኦሞዳ” እና “ጃይኮ” የተሰኙትና…