11
Oct
የብሪታኒያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ብሪታንያ መንግሥት ለኢትዮጵያ የ23 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቃለች፡፡ ከዚህ ውስጥ 16 ሚሊዮን ፓውንዱ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ከተሳተፉት ውስጥ የትግራይ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የእንግሊዝ መንግስት በኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፍን ለመደገፍ የሚውል እና ለሶስት አመታት የሚቆይ የ6 ነጥብ 9 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡ ድጋፉ ትግራይን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች የሚውል ሲሆን 7000 የሚሆኑ ሴት ሰራተኞችን ህይወት ለማሻሻል እና የወጭ ንግድን 20 በመቶ ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት በተካሄደው በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተሳተፉ ተዋጊዎችን ወደ ቀድሞ ህይወታቸው ለመመለስ በጀት በማሰባሰብ ለይ ስትሆን የአውሮፓ ህብረት 12 ሚሊዮን…