Carbonmarket

ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በካርበን ግብይት ውስጥ እንዲሳተፉ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በካርበን ግብይት ውስጥ እንዲሳተፉ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላንና ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይቷል። ረቂቅ አዋጁ የተበታተነውን የካርበን ግብይት በአንድ የሕግ ማዕቀፍ ለማስተዳደር እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ጅምር ስራዎችን ለማጠናከር እንደሚረዳ በውይይቱ ላይ ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ ለአየር ንብርት ለውጥ ተጋላጭ መሆኗን ያስታወሰው የካርበን ረቂቅ አዋጅ ለአማቂ ጋዝ ልቀት ቅነሳ ደጋፍ ማድረግ እና በአየር ንብርት ለውጥ ላይ አደገኛ ጣልቃ ገብነትን ማስቀረት "የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ነው" ብሏል። በአስር ክፍል እና በ44 ገጽ የተዘጋጀው ይህ የካርበን ግብይት ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ የተፈራረመችውን ስምምነት ለመተግበርም እንደሚረዳ በአላማዎቹ ስር ተጠቅሷል። ረቂቁ…
Read More