ዜና

በትግራይ ክልል ታዳጊዎች በሀይል ለውትድርና እየተመለመሉ መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ

በትግራይ ክልል ታዳጊዎች በሀይል ለውትድርና እየተመለመሉ መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እንዳስታወቀው ከሰኔ 17 ቀን 2018 ጀምሮ ደግሞ የግዳጅ ውትድርና ህግ ወጥቶለት ስራ ላይ መዋሉን ገልጿል። ይህ አዋጅ የዜጎችን ሰብአዊ መብቶችን የሚጥስ በመሆኑ እንዲቆም ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡ በትግራይ ክልል የግዳጅ ውትድርና ሰነድ ከመውጣቱ  አስቀድሞ በተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶችን በተለይም ሕጻናትን፣ ተፈናቃዮችን፣ የአእምሮ ጤና ሕሙማንን፣ እንዲሁም ከስደተኛ ካምፖችና ከጸበል ሥፍራዎች ጭምር በግዳጅ በማሰባሰብ ወደ ወታደራዊ ሥልጠና ካምፖች የማስገባት ተግባር ሲፈጸም እንደነበር ኢሰመኮ ተናግሯል፡፡ ኮሚሽኑ የግዳጅ ውትድርና ሰነዱ ከወጣ በኋላም ይህ ተግባር ይበልጥ ተጠናክሮ ቀጥሎ የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ከአብያተ ክርስትያናት፣ እንዲሁም በርካታ ሌሎች ሰዎችን ከገበያ ስፍራ፣ ከወጣቶች ማዘውተሪያ ማዕከላት እና ቤት ለቤት በሚደረግ አሰሳ በማፈስ ወደ ወታደራዊ ተግባር እንዲሰማሩ መደረጉን…
Read More
ኢትዮጵያ በአዲስ የብድር ስምምነት ዙሪያ እንድትጠነቀቅ የዓለም ባንክ አሳሰበ

ኢትዮጵያ በአዲስ የብድር ስምምነት ዙሪያ እንድትጠነቀቅ የዓለም ባንክ አሳሰበ

ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ከ460 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር ያፀደቀው የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ከአዳዲስ የብድር ጫና እንድትቆጠብ አስጠንቅቋል፡፡ ኢትዮጵያ ከእዳ ጫና እንድትላቀቅ በምትፈጽማቸው አዳዲስ የብድር ስምምነቶች ዙሪያ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ልትወስድ እንደሚገባ አስታውቋል። ተቋሙ አምስተኛውን የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ግምገማ ማጠናቀቁን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ተጨማሪ 464 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያ አጽድቋል። የተቋሙ የበጀት ድጋፍ ከሁለት አመት በፊት ያፀደቀውና ለአራት አመት በሂደት የሚለቀቅ በሚል የፈቀደው የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ብድር አካል ነው፡፡ የአይኤምኤፍ የስራ አመራር ቦርድ ያፀደቀው የ464 ሚሊዮን ዶላር ብድር እስካሁን በአራት ዙር ከተለቀቀው ሁሉ የላቀ ሲሆን ለወደፊቱ ከሚለቀቀው ብድር ታሳቢ የሚደረግ የ200 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ገንዘብ ታክሎበታል። ጭማሪ ገንዘቡ…
Read More
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ

መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት 80 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል። የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት፣ የተገኘው ትርፍ ባንኩ ባለፉት ጊዜያት ካጋጥሙት የህልውና አደጋ መውጣቱን ያሳያል ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ባንኩ ከስድስት ዓመታት በፊት ከነበረበት ችግር ወጥቶ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ደረጃ ቀዳሚ ከሚባሉ ጠንካራ ባንኮች ተርታ መሰለፉንም ተናግረዋል። ባንኩ ለደረሰበት ከፍተኛ የትርፍ መጠን በዋናነት ለግል ዘርፉ የሰጠው ትኩረት፣ የተበላሸ ብድር መጠን መቀነሱ እና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት መስፋፋትን በምክንያትነት አንስተዋል። ባንኩ እየተጠናቀቀ ባለው የዘንድሮው በጀት ዓመት 648 ቢሊዮን ብር አዲስ ብድር እንደሰጠም ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል። ከተሰጠው ብድር ውስጥም 90 በመቶ የሚሆነውን ወይም 588 ቢሊዮን ብር ለግል ዘርፍ መቅረቡም ተገልጿል።…
Read More
በህገወጥ የቡና አዘዋዋሪዎች ላይ የ50 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ቅጣት ተጣለ

በህገወጥ የቡና አዘዋዋሪዎች ላይ የ50 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ቅጣት ተጣለ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሀገሪቱ ዋነኛ የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ በሆነው የቡና ምርት ላይ የሚፈጸመውን ህገ-ወጥ ዝውውር (ኮንትሮባንድ) ለመግታት፣ ከተባባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥብቅ የሆኑ የቁጥጥርና የቅጣት እርምጃዎችን መተግበር መጀመሩን አስታውቋል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሰፊሳ አባቡ እንደተናገሩት ህገ-ወጥ የቡና ንግድ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በእጅጉ እየጎዳ በመሆኑ፣ ድርጊቱን ለመከላከል አዲስ የክትትል ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል። በዚህም መሠረት ባለስልጣኑ ህገ-ወጥ የቡና ዝውውርን ለማስቆም ከፌዴራልና ክልል ፖሊስ፣ ከጉምሩክ ባለስልጣን እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር የጋራ ግብረ-ኃይል አቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም ኋላፊው አክለዋል። በመሆኑም ያለ ህጋዊ ፈቃድና ሰነድ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም የቡና ምርት ሙሉ በሙሉ በመንግስት ይወረሳል ተብሏል። በህገ-ወጥ…
Read More
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አለም አቀፍ ሹመት አገኙ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አለም አቀፍ ሹመት አገኙ

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት እና አንጋፋ ዲፕሎማት የሆኑት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  አዲስ ሹመት ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡ ሹመቱን የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ እንደሰጡ ቢሮው በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል። ፕሬዝደንቷ የተመደቡት በምእራብ አፍሪካና ሳህል ቢሮ ውስጥ ገለልተኛ ስትራቴጂያዊ ግምገማ እንዲያደርጉ ሲሆን፣ ዋና ተግባራቸውም ተቋሙ ለአካባቢው ቀውሶች በሚሰጠው ዘገምተኛ ምላሽ ሳቢያ የሚነሱበትን ትችቶችና የአሰራር ክፍተቶችን መመርመር ነው።ወይዘሮ ሳህለወርቅ ከሀምሌ ወር ጀምሮ አዲሱን ሹመት ተቀብለው ስራ እንደሚጀምሩ ተገልጿል፡፡ ወይዘሮ ሳህለወርቅ ስራቸውን ከመጀመራቸው በፊት በመጀመሪያ ወደ ኒውዮርክ በማቅናት ከፀጥታው ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ይቀበላሉ የተባለ ሲሆን፣ በመቀጠልም የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ወደሚገኝበት ሴኔጋል ዳካር በመጓዝ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ይወያያሉ።ለቀድሞዋ ፕሬዝደንት ይህ…
Read More
ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በካርበን ግብይት ውስጥ እንዲሳተፉ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በካርበን ግብይት ውስጥ እንዲሳተፉ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላንና ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይቷል። ረቂቅ አዋጁ የተበታተነውን የካርበን ግብይት በአንድ የሕግ ማዕቀፍ ለማስተዳደር እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ጅምር ስራዎችን ለማጠናከር እንደሚረዳ በውይይቱ ላይ ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ ለአየር ንብርት ለውጥ ተጋላጭ መሆኗን ያስታወሰው የካርበን ረቂቅ አዋጅ ለአማቂ ጋዝ ልቀት ቅነሳ ደጋፍ ማድረግ እና በአየር ንብርት ለውጥ ላይ አደገኛ ጣልቃ ገብነትን ማስቀረት "የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ነው" ብሏል። በአስር ክፍል እና በ44 ገጽ የተዘጋጀው ይህ የካርበን ግብይት ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ የተፈራረመችውን ስምምነት ለመተግበርም እንደሚረዳ በአላማዎቹ ስር ተጠቅሷል። ረቂቁ…
Read More
ለአዲሰ አበባ ከተማ ዓመታዊ በጀት 502 ቢሊዮን ብር ተመደበ

ለአዲሰ አበባ ከተማ ዓመታዊ በጀት 502 ቢሊዮን ብር ተመደበ

ከተመደበው በጀት ውስጥ ትልቁን ድርሻ የያዘው ለድህነት ቅነሳና ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ በሚል የተመደበው ነው ተብሏል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ሰኔ 12፣ 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው፤ የከተማዋን የ2019 ዓ.ም ረቂቅ በጀትን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በዚህም መሰረት ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚጀምረው የ2019 በጀት ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ በጀት 502 ነጥብ 27 ቢሊዮን ብር ሆኖ ወደ ምክር ቤት እንዲመራ መመርያ ሰጥቷል ። ረቂቅ በጀቱ የከተማ አስተዳደሩን የልማት ስትራቴጂዎች እና የትኩረት አቅጣጫዎች፣ድህነትን ለመቀነስ፣ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማረጋገጥ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ተዘርዝሯል። በተጨማሪም የከተማውን ነዋሪ የልማት ፍላጎትና የአገልግሎት አቅርቦት ለማሳደግ በተለይም  የስራ እድል ፈጠራን ለሚያበረታቱ የመሰረተ…
Read More
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ

ዓለም ባንክ ከአንድ ወር በኋላ ለኢትዮጵያ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በጀት ድጋፍ ሊያጸድቅ መሆኑን ገልጿል። አንድ የባንኩ ከፍተኛ ባለሙያ ሲናገሩ አዲስ ማለዳ ሰምታለች። የገንዘብ ሚኒስቴር ከሳምንት በፊት የ2019 ዓ.ም የበጀት ረቂቀን ለምክር ቤቱ ባቀረበበት ወቅት ከ2.3 ትሪሊዮን ብር በላይ መሆኑን ገልፆ የበጀት ጉድለቱ ከውጭ እርዳታ እና ሀገር ውስጥ በሚገኝባቸው ገቢ ይሸፈናል ማለቱ ይታወሳል። በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ቢሮ የግሉ ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብስራት ተሾመ እንደገለጹት ከሆነ ባንኩ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚውል የአንድ ጊዜ የበጀት ድጋፍ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። ባለሙያው ይህን ያሉት ትናንት ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር ባዘጋጁት የውይይት መድረክ…
Read More
ጁንቱ ቴክኖሎጂ የ“ቼሪ” ምርቶችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ ጀመረ

ጁንቱ ቴክኖሎጂ የ“ቼሪ” ምርቶችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ ጀመረ

“ጁንቱ ቴክኖሎጂስ ግሩፕ” የ“ቼሪ” አውቶሞቢል ኩባንያ (Chery Automobile) ምርቶችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ መጀመሩን አስታወቀ፡፡  ድርጅቱ “ኦሞዳ” (OMODA E5) እና “ጃይኮ” (JAECOO J5) የተሰኙትንና የ“ቼሪ” ምርቶች የሆኑትን ሁለት የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎችን ለኢትዮጵያ ገበያ በማቅረብ የዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ወኪል አቅራቢነቱን ማስፋፋቱን ገልጿል፡፡   ድርጅቱ ስራውን በዓለም አቀፍ ደረጃ በታወቀ አገልግሎት፣ በላቀ ቴክኖሎጂ እና በረጅም ጊዜ የገበያ ኢንቨስትመንት ለመምራትም “የጁንቱ-ኦሞዳ-ጃይኮ” የምርት ማሳያ (ሾውሩም) እና የድህረ ሽያጭ አገልግሎት ማዕከሉን ሰሞኑን ስራ አስጀምሯል።  የጁንቱ ቴክኖሎጂስ ትሬዲንግ የኦሞዳ እና ጃይኮ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክንዴ መቻል፣ ጁንቱ ቴክኖሎጂስ ከሁለት ወራት በፊት አራት ዓይነት የ“ጂ.ኤ.ሲ” (GAC) የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎችን ለገበያ ማቅረቡን አስታውሰው፣ በቅርቡ ደግሞ “ኦሞዳ” እና “ጃይኮ” የተሰኙትና…
Read More
በአዲስ አበባ ለ153 ሺህ ውሾች የእብድ ውሻ ክትባት መስጠት ተጀመረ

በአዲስ አበባ ለ153 ሺህ ውሾች የእብድ ውሻ ክትባት መስጠት ተጀመረ

የግብርና ሚኒስቴር እንደገለጸው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ "የእብድ ውሻ በሽታ" እየተባለ የሚጠራውን በንክሻ እና ቡጭሪያ ወደ ሰዎች የሚተላለፍ በሽታን ለማስቀረት ያለመ ክትባት በመሰጠት ላይ መሆኑን አስታውቋል። በሽታው በሰዎች ላይ እስከ ሞት የሚያደርስ አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ "የውሻ እብደት"በሽታን ለመከላከል 150 ሺህ ውሾችን ለመከተብ ዕቅድ ይዞ እየሰራ እንደሆነም ሚንስቴሩ አስታውቋል። ከሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም የጀመረው ይህ ዘመቻ ለእንስሳቱ የቤት ለቤት ክትባት መስጠትን አላማ ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል። ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም በሀገር አቀፍ ደረጃ ባከናወነው መደበኛ ክትባት ከ100 ሺህ በላይ ውሾችን የከተበ ሲሆን፤ ዘመቻው የውሻ እብደትን ከመከላከል ባለፈ የሰዎችን ደህንነት መጠበቅን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የእንስሳት ጤና መሪ ሥራ አስፈጻሚው ዶክተር ሲሳይ ጌታቸው ተናግረዋል።…
Read More